ሠላሣ አንደኛ ዓመት ቍጥር ፭
የ ኢ ት ዮ ጵ ያ ን ጉ ሠ ነ ገ ሥ ት መ ግ ሥ ት "
ነ ጋ ሪ ት ፡ ጋ ዜ ጣ ። ጋ
የጋዜጣው ዋጋ ባገር ውስጥ ባመት $ 6.
በ፮ ወር
ለውጭ አገ እጥፍ ይሆናል ።
ማውጫ "
፲፱፻፷፬ ዓ. ም.
በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት
በጽሕፈት ሚኒስቴር ተጠባባቂነት የቆመ
የሕግ ክፍል ማስታወቂያ ቍጥር ፬፻፲፬ / ፲፱፻፷፬ ዓ. ም.
የኤርትራ የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ቦርድ ማቋቋሚያ ደንብ
ቊጥር ፬፻፲፬ / ፲፱፻፷፬ ዓ. ም.
የሕግ ክፍል ማስታወቂያ ፤
በ፲፱፻፶፮ ዓ. ም. ስለ አሠሪና ሠራተኛ በወጣው አዋጅ መሠረት የወጣ ደንብ
፩ አውጪው ባለሥልጣን ፤
የሕዝባዊ ኑሮ ዕድገትና የማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
ይህን ደንብ ያወጣው በ፲፱፻፶፮ ዓ. ም. በቊጥር ፪፻፲ በወጣው (ከዚህ በኋላ « አዋጅ » እየተባለ በሚጠራው) የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ በአንቀጽ ፫ (ለ) በተሰ ጠው ሥልጣን መሠረት ነው ።
፪ / አጭር አርእስት ፤
ይህ ደንብ « የ፲፱፻፷፬ ዓ. ም. የኤርትራ ሪና ሠራ ተኛ ጉዳይ ቦርድ ማቋቋሚያ ደንብ » ተብሎ ሊጠቀስ ይቻላል ።
፫ ስለቦርዱ መቋቋም ፤
(፩) ኤርትራ ጠቅላይ ግዛት በሚገኘው የሕዝባዊ ኑሮ ዕድገትና የማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ውስጥ (ከዚህ በታች « ቦርድ » ተብሎ የሚጠራ) የአ ሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ቦርድ ተቋቁሟል ። (፪) ቦርዱ በኤርትራ ጠቅላይ ግዛት ውስጥ የሚነሡትን የሥራ ክርክሮችና ተገቢ ስላልሆነ የሥራ አፈጻጸም የሚቀርቡትን አቤቱታዎች ይሰማል ።
(F) የቦርዱ ዋና መሥሪያ ቤት በአሥመራ ይሆናል ። ሆኖም ቦርዱ አስፈላጊ መስሎ ከታየው በኤርትራ ጠቅላይ ግዛት ውስጥ በሚገኙ በሌሎችም ሥፍራዎች ለመሰብሰብ ይችላል ።
አዲስ አበባ ታኅሣሥ፯ ቀን ፲፱፻፷፬ ዓ. ም.
ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ ይታተማል "
የፖስታ ሣጥን ቍጥ G ፩ሺ፫፻፷፬ (1364)
፬ ቦርዱ በአዋጁ ከተቋቋመው የአሠሪና ሠራተኛ ቦርድ 4 ጋር እኩል ስለመሆኑ ፤
(፩) ቦርዱ በአዋጅ ለተቋቋመው የአሠሪና ሠራተኛ ቦርድ በአዋጁ እንደተሰጡት ያሉ ሥልጣኖችና ተግባሮች ይኖሩታል "
| Community Development and Social Affairs pursuant to autho rity vested in him by Article 3 (b) of the Labour Relations Pro
Equialence