የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አራተኛ ዓመት ቁጥር ፭ አዲስ አበባ ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፲ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፲፱የ3 ዓም የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣ ማሻሻያ ) . . . . . ገጽ ፮፻፵፯ አዋጅ ቁጥር ፮ / ፲፱፻፲ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ለማሻሻል የወጣ አዋጅ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ማሻሻል በማስፈለጉ ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈ | 1 . Short Title ጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣ ( ማሻሻያ ) አዋጅ ቁጥር ዥ ፲፱፻፲ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፴፯ ከአንቀጽ ፳፮ ንዑስ አንቀጽ ፲ ቀጥሎ የሚከተሉት አዲስ ንዑስ አንቀጾች ( ፲፩ ) እና ( ፲፪ ) ተጨምረው ተሻሽሏል ፣ ያንዱ ዋጋ 2 : 30 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፱ሺ፩ ገጽ ፮የሣቿ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፭ ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፲ ዓም “ ፲፩ ) የመከላከያ ተቋማት በሰላም ጊዜ የሚኖራቸውን የማምረትና አገልግሎት የመስጠት ትርፍ አቅም ለገቢ ማስገኛ ተግባር እንዲውል በማድረግና ለመከላከያ ጠቀሜታ የማያስፈልጉ ንብረቶችን በማስወገድ የሚገኘውን ገቢ እንዲሁም በተቆጣ ጣሪ ባለሥልጣንነት እንዲመራቸው ከተሰየመላቸው የመከላ ከያ ኢንዱስትሪ ድርጅቶች የሚገኘውን የትርፍ ድርሻ የሚኒስ ትሮች ምክር ቤትን እያስፈቀደ ለሀገር መከላከያ አቅም ግንባታ እንዲውል ያደርጋል ፲፪ ) የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፲፩ ) ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ የገንዘቡ አስተዳደር በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት የፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር ፵፯ ፲፱፻ዥሀ እና በአዋጁ መሠረት በወጡ ደንቦችና መመሪያዎች የተደነገጉትን ሥርዓቶችና መመዘኛዎች ተከትሎ መፈጸሙን ያረጋግጣል ፣ በዋናው ኦዲተርም እንዲመረመር ያደርጋል ። ” ፫ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፲ ዓም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፲ ዓም | ዶ ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤትታተመ