የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ስድስተኛ ዓመት ቁጥር ፴፯ አዲስ አበባ ሰኔ ፳ ቀን ፲፱፻፵፪ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነትወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፯ / ፲፱፻፪ ዓም . የፌዴራል ፖሊስ አዋጅ ገጽ ፩ሺ፫፻፴፩ አዋጅ ቁጥር ፪፻፯ / ፲፱፻፵፪ የፌዴራል ፖሊስን አደረጃጀትና አስተዳደር ለመወሰን የወጣ አዋጅ ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ታማኝና በሕገ መንግሥቱ መሠረት ለሚወጡ ሕጎች ተገዢ የሆነ ፡ ለሙያው በቂ የሆነ ሥልጠና የተሰጠውና ብቃት | police institution which is loyal to the Constitution of the ያለው ፡ ለሕዝብ አገልጋይና ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን | Federal Democratic Republic of Ethiopia and governed by የሚያከብርና የሕዝብን ሰላምና ደህንነት የሚያረጋግጥ የተጠናከረ | laws enacted in accordance with to the Constitution that has ሲቪል የፖሊስ ተቋም እንዲኖር ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ ፡ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፯ ) እና ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ክፍል አንድ አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የፌዴራል ፖሊስ አዋጅ ቁጥር ፪፻፯ / ፲፱፻፶፪ ” | 1. Short Title ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ በዚህ አዋጅ ውስጥ “ ሚኒስትር ” ወይም “ ሚኒስቴር ” ማለት | 2. Definition እንደቅደም ተከተሉ የፍትሕ ሚኒስትር ወይም የፍትሕ ሚኒስቴር ነው ። ክፍል ሁለት ስለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን መቋቋም ፩ . የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ከዚህ በኋላ “ ኮሚሽኑ ” እየተባለ የሚጠራ በዚህ አዋጅ ራሱን የቻለ የሕግ ሰውነት ያለው የፌዴራል አካል ሆኖ ተቋቁሟል ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖ.ሣቁ. ፱ሺ፩ ገጽ ፭ሺ'የ ደ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፯ ሰኔ ፳ ቀን ፲፱፻፲፪ ዓ.ም Federal Negarit Gazeta No.37 27 June , 2000 – Page 1332 ፪ ኮሚሽኑ በሕግና በሙያ የሚኖረው ነጻነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ተጠሪነቱ ለሚኒስቴሩ ይሆናል ። የኮሚሽኑ ዋና መሥሪያ ቤት የኮሚሽኑ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ሆኖ እንደአስፈላ ጊነቱ፡ በሌላ ማናቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤት ይኖረዋል ። ፭ . የኮሚሽኑ ዓላማ የኮሚሽኑ ዓላማ የሀገሪቱን ሕገ መንግሥትና ሌሎች ሕጎች በማክበር የሕዝቡን ተሳትፎ መሠረት በማድረግ ወንጀልን በመከላከል የሕዝብን ሠላማዊ ኑሮና ፀጥታ ማስጠበቅ ነው ። ፮ . የኮሚሽኑ ሥልጣንና ተግባር ኮሚሽኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፣ ፩ . ማንኛውንም ወንጀል የመከላከል ፡ ፪ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ሥልጣን ሥር የሚወድቁ ወንጀሎችን የመመርመር ፡ በሕግ የዳኝነት ሥልጣን ባላቸው ፍርድ ቤቶች የሚሰ ጠውን ትዕዛዝ ወይም ውሳኔ የመፈጸም ፡ • የወንጀል ምርመራን በተመለከተ ከፌዴራል ዐቃቤ ሕግ የሚሰጠውን ትዕዛዝ የመፈጸም፡ የጠረፍ ደህንነትን : የአየር ማረፊያዎችን ፡ የባቡር መስመሮችንና ተርሚናሎችን : የማዕድን ማውጫ ቦታዎችን ፡ ዋና ዋና የፌዴራል መንግሥት ተቋሞችን የመጠበቅ ፡ ፮ በድንገተኛ አደጋ ጊዜ ዕርዳታ የመስጠትና ከሚመለከ ታቸው ጋር የመተባበር ፡ ፯ ለከፍተኛ የፌዴራሉ መንግሥት ባለሥልጣናትና ለውጭ አገር እንግዶች ጥበቃ የማድረግ ፡ ለክልል የፖሊስ ኮሚሽን የሥልጠና ፡ የሙያና የቴክኒክ ምክርና ድጋፍ የመስጠት ፡ እንዲሁም በክልሎች ጥያቄ ሲቀርብ የክልል የወንጀል ጉዳዮችን ለመከላከልና ለመ መርመር እገዛ የማድረግ : ሀ . ከወንጀል ነጻ የመሆንን ማስረጃ የመስጠት ፡ የወንጀል መነሻ ምክንያቶችን በማጥናት የመከላከል ዘዴዎችን የመንደፍ፡ ፡ ፲፩ . የፌዴራል ወንጀል የመመርመር ሥልጣን እንደአስፈላ ጊነቱ ለክልል የፖሊስ ኮሚሽን በውክልና የመስጠት ፡ ፲፪- የወንጀል መረጃዎችንና ስታትስቲክሶችን የማሰባሰብ ፡ የማጥናትና የማሰራጨት እንዲሁም የወንጀል መረጃዎች ማሰባሰቢያና ማጠናከሪያ ሀገር አቀፍ ሥርዓት የማቋቋም : • አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለሌሎች አካላት ወይም ለሲቪል የመንግሥት ሠራተኞች የተወሰኑ ሥራዎችን ለማከናወን የሚያስችል የፖሊስ ሥልጣን የመስጠት ፡ 10- ለፌዴራሉና ለክልል አካላት የቴክኒክ ምርመራዎች ማከናወንና ምስክርነት የመስጠት ፡ 12 : - ከአለም አቀፍ ፖሊስ ጋር ግንኙነት በመፍጠር የመረጃ ልውውጥ የማደረግ ፡ 1 ጌ ውል የመዋዋል : የንብረት ባለቤት የመሆን : በስሙ የመክሰስና የመከሰስ ። ጊ የኮሚሽኑ አቋም ኮሚሽኑ ፡ አንድ የኮሚሽነሮች ጉባኤ ( ከዚህ በኋላ “ ጉባኤው ” | 7 . Organization of the Commission እየተባለ የሚጠራ ) ፡ ኣንድ ኮሚሽነር ፡ ምክትል ኮሚሽነሮች ፡ • ረዳት ኮሚሽነሮች ፡ ፭ ሌሎች የፌዴራል ፖሊሶች ፡ ፮ አስፈላጊ የሆኑ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ፡ ይኖሩታ ል ። ፭ የፌዴራል ፖሊስን የሥራ ብቃትራ ረገጥ ገጽ ፩ሸ r ያ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፯ ሰኔ ፳ ቀን ፲፱፻፵፪ ዓ.ም. ፲ የገባኤው አባላት የጉባኤው አባላት ፩ ኮሚሽነሩ ፪ ም / ኮሚሽነሮች - ረዳት ኮሚሽነሮች ይሆናሉ ። ሀ . የኮሚሽነሮች ጉባኤ ሥልጣንና ተግባር የኮሚሽነሮች ጉባዔ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፡ ፩ . የኮሚሽኑን የሥራ እንቅስቃሴ በበላይነት ይመራል ፡ ያስተባብራል ፡ ፪ • የኮሚሽኑን ም ኮሚሽነሮችና ረዳት ኮሚሽነሮች ሹመት እንዲፀድቅለት ለሚኒስቴሩ ያቀርባል ፡ | የኮሚሽኑን የሥራ ብቃትና ውጤታማነት ለማሳደግ አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል ፡ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፩ ንዑስ አንቀጽ ( ) ( ሐ ) መሠረት ተጣርተው በሚቀርቡ አቤቱታዎች ላይ ውሳኔ ይሰጣል ፡ ፭ . የኮሚሽኑን ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም በመገምገም ከአስ ተያየት ጋር ለሚኒስቴሩ ያቀርባል ፡ የፌዴራል ፖሊስን የሥራ ብቃት ለማረጋገጥ የኢንስፔ ክሽን ሥራ ያከናውናል ፡ ጊ የኮሚሽኑን ረቂቅ በጀት አዘጋጅቶ ለሚኒስቴሩያቀርባል፡ ሲፈቀድም አፈጻጸሙን ይከታተላል ፡ ፲ አዋጁን ለማስፈጸም የሚረዱ ረቂቅ ሕጎች አዘጋጅቶ ለሚኒስቴሩ ያቀርባል ፡ ፱ በኮሚሽኑ እና በክልል ፖሊስኮሚሽን መካከል መልካም የሥራ ግንኙነት እንዲኖር ጥረት ያደርጋል ፡ | ይህን አዋጅና በዚህ አዋጅ መሠረት የሚወጡ ደንቦችን ለማስፈጸም የሚረዱ መመሪያዎችን ያወጣል ፡ በሥራ ላይ መዋላቸውንም ያረጋግጣል ። † የሚኒስቴሩ ሥልጣንና ተግባር ሚኒስቴሩ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፡ ፩ ኮሚሽኑን በበላይነት ይመራል ፡ ይቆጣጠራል ፡ ፪ የኮሚሽኑን ምክትል ኮሚሽነሮች እና ረዳት ኮሚሽነሮች ይሾማል ፡ የኮሚሽኑን የሥራ ብቃትና ውጤታማነት ለማሳደግ አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል ፡ ፬ . የኮሚሽኑን ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ለመንግሥት ያቀርባል ፡ ፮ የኮሚሽኑን ረቂቅ በጀት ለመንግሥት ያቀርባል : ሲፈቀድም አፈጻጸሙን ይከታተላል ፡ ፮ አዋጁን ለማስፈጸም የሚረዱ ረቂቅ ሕጎች ለመንግሥት ያቀርባል ። ፲፩ ስለኮሚሽነር ኮሚሽነሩ በሚኒስትሩ አቅራቢነት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሾማል ' ። ፪ • ኮሚሽነሩ የኮሚሽኑን የሥራ እንቅስቃሴ የማስተባበርና አመራር የመስጠት ሥልጣንና ተግባር ይኖረዋል ። ፫ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፪ ኣጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ኮሚሽነሩ ፡ ሀ ) የፌዴራል ፖሊስን መተዳደሪያ ደንብ ያስፈጸማል ፡ ለ ) በፌዴራል ፖሊስነት ከተቀጠሩት ውጭ ያሉትን የድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግ መሠረት ይቀጥራል ፡ ያስተዳድራል ፡ ሐ ) በፌዴራል ፖሊስ ላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎች እንዲጣሩ በማድረግ ለኮሚሽነሮች ጉባኤ እንዲ ቀርብ ያደርጋል : ጉባዔው የሰጠውንም ውሳኔ ለአቤቱታ አቅራቢው ያስታውቃል ፡ ገጽ ፩ሺ ፻፴፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፯ ሰኔ ፳ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓም Federal Negarit Gazeta No.37 27 June , 2000 - Page 334 የኮሚሽኑን ዓመታዊ የሥራ ፕሮግራምና ረቂቅ በጀት ያዘጋጃል ፡ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፡ ሠ ) ለኮሚሽኑ በተፈቀደው በጀት መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፡ ረ ) ኮሚሽኑ ከሶስተኛ ወገኖች ጋር በሚያደርገው ግንኙነት ሁሉ ኮሚሽኑን ይወክላል ። 0 ኮሚሽነሩ ለኮሚሽኑ የሥራ ቅልጥፍና ባስፈለገ መጠን ከሥልጣንና ተግባሩ በከፊል ለምክትል ኮሚሽነሮች ወይም ለረዳት ኮሚሽነሮች ወይም ለሌሎች ሠራተኞች በውክልና ሊሰጥ ይችላል ። ፲፪- በጀት የኮሚሽኑ በጀት በፌዴራል መንግሥት ይመደባል ። ፲፫ . ስለሂሣብ መዛግብት ፩ ኮሚሽኑ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብት ይይዛል ። ፪ የኮሚሽኑ የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም ዋናው ኦዲተር በሚሰይመው ኦዲተር በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ክፍል ሶስት ስለፌዴራል ፖሊስ አስተዳደር ፲፬ . ለፖሊስነት የሚያበቁ መመዘኛዎች ፩ . ማንኛውም የኢትዮጵያ ዜጋ በፌዴራል ፖሊስነት ለመ መልመል የሚከተሉትን መመዘኛዎች የሚያሟላ መሆን ይኖርበታል ፡ ሀ ) በፖሊስነት ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ ፡ ለ ) ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት ታማኝ የሆነ ፡ ሐ ) በፌዴራል ፖሊስነት ለመመልመል የሚያስፈል ገውን የትምህርትደረጃና አካላዊ ብቃት የሚያሟላ፡ መ ) በህብረተሰቡ ውስጥ በዲሲፕሊኑ ወይም በሥነ ምግባሩ መልካም ስም ያተረፈ ፡ ሠ ) ከዚህ ቀደም በወንጀል ድርጊት ውስጥ ለመሣተፉ ሪኮርድ የሌለበት ፡ ረ ) ዕድሜው ከ፲፰ ዓመት ያላነሰ ፡ ሰ ) የማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆነ ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት የሚደረገው ምልመላ የፆታ ፡ የብሔሮች ፣ ብሔረሰቦችና የሕዝቦችን ሚዛናዊ ተዋጸኦ ያካተተ ይሆናል ። • የፖሊስ ምልመላ በሕዝብ ተሳትፎ ላይ የተመሠረተ ይሆናል ። ፲፭ ቃለ መሐላ ስለመፈጸም በፌዴራል ፖሊስነት የተመለመለ የተጣለበትን ሕዝባዊና ሙያዊ አደራ በታማኝነትና በታታሪነት ለመወጣት ቃለ መሐላ ይፈጸማል ። ፲፮ ለሲቪል የመንግሥት ሠራተኞች የፖሊስ ሥልጣን ስለመ ልዩ ሙያ ለሚጠይቁ ጉዳዮች ለሲቪል የመንግሥት ሠራተኛ የፖሊስ ሥልጣን ሊሰጥ ይችላል ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት የሚሰጠው የፖሊስ ሥልጣን ለጉዳዩ አስፈላጊ በሆነው መጠን ብቻ ይሆናል ። ፲፯ የአገልግሎት ዘመን የማንኛውም የፌዴራል ፖሊስ አባል የግዴታ አገል ግሎት ዘመን ሰባት ዓመት ይሆናል ። ዝርዝር አፈጻጸሙ በደንብ ይወሰናል ። ፪ . የማንኛውም የፌዴራል ፖሊስ አባል የግዴታ ኣገል ግሎት በሚከተሉት ምክንያቶች ይቋረጣል ፡ ገጽ ፭ሺ፫፻፴፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፯ ሰኔ ፳ቀን ፲፱፻፶፪ ዓም Federal Negarit Gazeta No.37 27 June , 2000 - Page 1335 ሀ ) በሞት፡ ለ ) የስንብት ጥያቄ ቀርቦ በደንቡ መሠረት ተቀባይነት ሲያገኝ : ሐ ) በሓኪሞች ቦርድ በተረጋገጠ ሕመም ለሥራው ብቁ ሳይሆን ሲቀር ፡ መ ) በፍርድ ቤት በወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘና ወንጀሉ ለሥራው ብቁ አያደርገውም ተብሎ በኮሚሽኑ ሲወሰን ፡ ዝርዝሩ በሚወጣው ደንብ ይወሰናል ፡ ሠ ) በሥራ አፈጻጸም ወይም በአመራር ብቁ ባለመሆን ወይም በዲሲፕሊን ጥፋት ፡ ረ ) በጡረታ ሲገለል ። ፲፰ መብት ፩ . ማንኛውም የፌዴራል ፖሊስ አባል ፡ ሀ ) በመንግሥት በሚጸድቅ የደመወዝ ስኬል መሠረት ደመወዝ ያገኛል ፡ ለ ) በኮሚሽኑ የመተዳደሪያ ደንብ መሠረት ቀለብ ፡ ልዩ ልዩ አበሎች የደንብ ልብስናየሕክምና አገልግሎት ያገኛል ፡ ሐ ) በጡረታ ሕግ መሠረት የጡረታ መብት ይኖረዋል ፡ ሥራውን በተገቢው መንገድ በመወጣት ላይ እያለ ለሚደርስበት ተጠያቂነት መሥሪያ ቤቱ ጠበቃ ያቆምለታል አፈጻጸሙ ይወሰናል፡ በማንኛውም አጋጣሚ ኃላፊዎችን በአግባቡ የመጠየቅ : ስህተት ሲያይ የመጠቆም በውይይት ችግሮችን የመፍታት መብት አለው : አስፈላጊም ሲሆን የሥልጣን ተዋረድን ጠብቆ አቤቱታ ማቅረብ ይችላል ፡ ረ ) ከሥራው ጋር በተያያዘ ሁኔታ ለሚደርስበት የሕይወት ወይም የአካል ጉዳት ወደፊት በሚወጣው ደንብ መሠረት የካሣ ክፍያ ያገኛል ። ፪ . ከላይ ከተገለጹት መብቶች በተጨማሪ በፌዴራል ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስነት ተመድበው ለሚሠሩ አባሎች ኮሚሽኑ የመኖሪያ ካምፕ ያዘጋጅላቸዋል ። በዚህ አዋጅ ከተመለከቱት ውጭ ያሉ መብቶችን በተመ ለከተ የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግ ተፈጻሚ ይሆናል ። ፲፱ . ግይታ ማንኛውም የፌዴራል ፖሊስ ፡ በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጡትን ሰብዓዊና ዲሞክራ ሲያዊ መብቶች ሳይሸራርፍበማክበር በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግና በሌሎች አግባብ ባላቸው ሕጎች መሠረት ሥራውን የማከናወን ፡ ፪ ፖሊሳዊ ሥራውን ሲያከናውን ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ የማሳየት ፡ ግዴታ አለበት ። ፳ • የጡረታ መውጫ ዕድሜ ማንኛውም የፌዴራል ፖሊስ አባል በጡረታ የሚገለልበት ዕድሜ ጣሪያ ፶፭ ዓመት ይሆናል ። ፳፩ . ወታደራዊማዕረግ ስለመቅረቱ ፩ በማንኛውም ደረጃ የሚገኝ የፌዴራል ፖሊስ ወታደራዊ ማዕረግ አይኖረውም ፡ ሆኖምግን ይህን የሚተካየፖሊስ የሆነ ማዕረግና ምልክት ይኖራል : ዝርዝሩ በደንብ ይወሰናል ። ፪ የፌዴራል ፖሊስ አባል የሥራ መደቡን የሚያመለክት የመለያ ደንብ ልብስ ፡ እንዲሁም ማንነቱን የሚገልጽ ስም : ቁጥር : ክፍሉንና ኃላፊነቱን የያዘ ባጅ ወይም ምልክት ይኖረዋል ። ገጽ ፭ሺ፫፻፴፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፯ ሰኔ ፳ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓም ፳፪ አሠራር ፩ በፌዴራል ፖሊስ መዋቅር በየደረጃው ባሉትኃላፊዎችና | 22. Performance ሠራተኞች የቡድን አሠራር ዋና የተግባር አፈጻጸም አቅጣጫ ይሆናል ። ፪ በፌዴራል ፖሊስ መዋቅር በየደረጃው የሚገኙኃላፊዎች በተሰጣቸው በመወሰን ኃላፊነታቸውን የመወጣት ግዴታ አለባቸው ። ፫ . ከሥራ ዕቅድ አነዳደፍ እስከ አፈጸጸምና ግምገማ ድረስ የፌደራል ፖሊስ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በቡድን በመቀ ናጀት ይሠራሉ : የቡድን አሠራሮች የጋራና የግል ላፊነትን ያስከትላሉ ። የፖለስ አሠራር የሕዝብ ተሳትፎን መሠረት ያደረገ መሆን ይኖርበታል ። ፳ • የተከለከለ ድርጊት ማናቸውም ኢሰብአዊ ወይም ክብርን የሚነካ አያያዝና | 23. Prohibited Activities ድርጊት የተከለከለ ነው ። ፳፬- ስለፌዴራል ፖሊስ አቤቱታ ሰሚ ፩ በኮሚሽኑ ውስጥ የፌዴራል ፖሊስ አቤቱታ ሰሚ አካል ይቋቋማል ። ፪ . የፌዴራል ፖሊስ አቤቱታ ሰሚ አካል ፡ የፌዴራል ፖሊስ በኮሚሽኑ አካላት ሥራ አፈጻጸም ወይም አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከግለሰብ ፡ ከመሥሪያ ቤት : ከድርጅት ወይም ከሕዝብ የሚቀርብ አቤቱታ : አስተያየትን ወይም ትችትን ይቀበላል ፡ ያጣራል ፡ በሚቀርብለት አቤቱታ መነሻነት ማናቸውንም የፌዴራል ፖሊስ አባል ስለአቤቱታው መልስ እንዲሰጥ ያደርጋል ፡ ሐ ) የቀ አቤቱታ ፡ አስተያየት ወይም ትችት በማጣራት መወሰድ ስለሚገባው እርምጃ ያለውን ኣስተያየት ለኮሚሽነሩ ያቀርባል ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፪ ( ለ ) መሠረት መልስ እንዲሰጥ የተጠየቀየፌዴራል ፖሊስ አባል በ፲፭ ቀን ጊዜ ውስጥ መልስ የመስጠት ግዴታ አለበት ። ክፍል አራት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፳፭ ኮሚሽኑ ከክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች ጋር ስለሚኖረው ግንኙነት ፩ ኮሚሽኑ የፌዴራል ጉዳዮችን በሚመለከት ከክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች ጋር ግንኙነት ይኖረዋል ። ፪ የክልል ፖሊስ መሥሪያ ቤቶች በውክልና መሠረት የፌዴራል ወንጀል ጉዳዮችን ሲመረምሩና ሲከላከሉ ተጠሪነታቸው ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ይሆናል ። ፫ ኮሚሽኑና የክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች በዓመት ቢያንስ ኣንድ ጊዜ የጋራ ስብሰባ ያደርጋሉ ። • ኮሚሽኑ ለክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች ሥልጠና ፡ የሙያና የቴክኒክ ምክርና ድጋፍ ያደርጋል ። የክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች ወንጀልን : ትራፊክንና ፀጥታን በሚመለከት ሪፖርትና ስታትስቲክስ ለጥናትና ለወል ጠቀሜታ እንዲውል በየጊዜው ለኮሚሽኑ ሪፖርት ያስተላልፋሉ ። በኮሚሽኑና በክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች የጋራ ስብሰባ የሚከተሉት ተግባሮች ይከናወናሉ ፡ ሀ ) የወንጀል መከላከልና ምርመራ ሥራ እንቅስቃሴዎ ቻቸውን በመገምገም የልምድ ልውውጥ ያደርጋሉ ፡፡ ገጽ ፭ሺ፫፻፴፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፯ ሰኔ ፳ ቀን ፲፱፻፶ ዓም ለ ) የጋራ የወንጀል መከላከል አቅጣጫዎችን ይቀይ ሳሉ፡ ይወስናሉ ፡ ሐ ) አንድ ወጥ መመዘኛየሚያስፈልጋቸውን ፖሊስነክ ጉዳዮች በጋራ ይለያሉ ፡ መመዘኛውንም በጋራ ያወጣሉ : አፈጻጸሙን በጋራ ይገመግማሉ ። ፳፮ የተሻሩና ተፈጻሚነት የማይኖራቸው ሕጎች ፩ የሚከተሉት በዚህ አዋጅ ተሽረዋል ፡ ሀ ) የፖሊስ ኃይል ማደራጃ አዋጅ ቁጥር ፩ / ፲፬፻፴፬ ለ የፖሊስ ሠራዊት መኰንኖች አስተዳደር ትዕዛዝ ሐ ) የፖሊስ ሠራዊት መኮንኖች የማዕረግ እድገት አሰጣጥ ፡ የግዴታ አገልግሉትና የማስወጣ ደንብ ቁጥር ፬፻፴ / ፲፱፻፳፭ ፡ እና መ ) ስለማዕከላዊ የሽግግር መንግሥት የአገር መከላከያ ሠራዊት ስምሪትና ስለፖሊስ ኃይል መቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር ፰ / ፲፱፻፳፬ ዓም ፖሊስን የሚመለከቱት ድንጋጌዎች ። ፪ ከዚህ አዋጅጋር የሚቃረን ማናቸውም ሕግተፈጻሚነት አይኖረውም ። ፳፯ ደንብ የማውጣት ሥልጣን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ይህን አዋጅ ለማስፈጸም ደንብ የማውጣት ሥልጣን ይኖረዋል ። ፳፰ አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ካሰኔ ፳ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ሰኔ ፳ ቀን ፲፱፻፪ ዓም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰምተህርታቱም