የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ
ሦስተኛ ዓመት ቁጥር ፲ 0 አዲስ አበባ ታኅሣሥ ፲ ቀን ፲፱፻፳፱
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ
አዋጅ ቁጥር ዛጊ ሀየዝህ ዓም . የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥት የፋይናንስ አስተዳደር
ገጽ ፪፻፲፰
አዋጅ ቁጥር ሃጊ ፲፱፻፳፱ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥት የፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ
መንግሥት ኃላፊነቱን በትክክል መወጣት እንዲችል ዘመናዊ እና ቀልጣፋ የፋይናንስ አስተዳደር ሥርዓት መዘርጋት ያለበት በመሆኑ ፡
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥት የፋይናንስ አስተዳደር የሚመራበትን መሠረታዊ ጽንሰ ሃሳብ ፡ መርህ እና ዋና ዋና ጉዳዮች መወሰን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፡
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ።
ክፍል አንድ
፩ . አጭር ርዕስ
ይህ አዋጅ “ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥት የፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር ሃጊ በህየሸህ ” ተብሎ ሊጠቀስ
ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ
በዚህ አዋጅ ውስጥ፡ ፩ . “ በዓይነት የተሰጠ እርዳታ ” ማለት የፌዴራል
መንግሥት ከገንዘብ ሌላ በዕቃ ወይም በአገልግሎት መልክ በሁለት ወይም በባለብዙ ወገን ስምምነት ወይም
ከሌሎች ምንጮች የሚቀበለውማናቸውም እርዳታ ነው፡ ፪ • “ መፍቀድ ” ማለት ከተጠቃለለው ፈንድ ላይ ለመክፈል
የሚያስችል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚሰጥ ማናቸውም ሥልጣን ነው :
ነጋሪት ጋዜጣ ፖ.ሣ.ቁ : ዥሺ፩
ያንዱ ዋጋ