የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ
አስራ አራተኛ ዓመት ቁጥር ፳፯ አዲስ አበባ ሚያዝያ ፲፮ ቀን ፪ሺ
ደንብ ቁጥር ፩፻፱ / ፪ሺ
? ቃሊቲ ኮንስትራክሽንና የኮንስትራክሽን ዕቃዎች ማምረቻ ድርጅት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ገጽ ‥ ፬ሺ፷፫
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፵፱ / ፪ሺህ የቃሊቲ ኮንስትራክሽንና የኮንስትራክሽን ዕቃዎች ማምረቻ ድርጅትን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻፹፬ አንቀጽ ፵፯ / ፩ (ሀ) መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል:: ፩. አጭር ርዕስ
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ADDIS ABABA - 24th April 2008 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ
ይህ ደንብ “ የቃሊቲ ኮንስትራክሽንና የኮንስትራክሽን ዕቃዎች ማምረቻ ድርጅት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፵፱ / ፪ሺ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል::
፪ መቋቋም
፩. የቃሊቲ ኮንስትራክሽንና የኮንስትራክሽን ዕቃዎች ማም ረቻ (ከዚህ በኋላ “ ድርጅት ” እየተባለ የሚጠራ) የመንግ ሥት የልማት ድርጅት ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ፡፡
፪. ድርጅቱ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻፹፬ መሠረት ይተዳደራል ፡
፫ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን
የሃገር መከላከያ ሚኒስቴር የድርጅቱ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ይሆናል::
ያንዱ ዋጋ
ፖ.ሣ.ቁ. ፹ሺ፩