የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ : : ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አምስተኛ ዓመት ቁጥር ፲፬ አዲስ አበባ ኅዳር ፲፭ ቀን ፲፱፻፲፩ | በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፩፻፴፯ / ፲፱፻፲፩ ዓ ም የማዳበሪያ ማምረትና ንግድ አዋጅ . . . . . . . . . . . . . . . ገጽ ፰፻፱ አዋጅ ቁጥር ፩፻፴፯ / ፲፱፻፲፩ የማዳበሪያ ማምረትና ንግድ ድርጅት አዋጅ የአገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት መሠረት የሆነውን ግብርናን | _ በዘመናዊ የእርሻ ሳይንስና በምርት ግብአቶች ማጐልበት በማስ | ፈለጉ ፡ ማዳበሪያ ለግብርናው ክፍለ ኤኮኖሚ ወሳኝ ግብአት በመሆኑ ወቅታዊ አቅርቦቱ ፡ ጥራቱን ፡ ግብይቱን ፡ በተፈለገው ቦታናመጠን መሠራጨቱንና መሸጡን በቅርብ መከታተልና ሥርዓት ማስያዝ | marketing , distribution and selling of fertilizer to the required አስፈላጊ በመሆኑ ፡ ማዳበሪያ ልዩ ጥንቃቄ የሚሻ ኬሚካላዊ ቁስ በመሆኑ በአመራረት ፡ በማስመጣት ፡ በአያያዝና በአከመቻቸት ደረጃውን የጠበቀ ለመሆኑ ቁጥጥርና ክትትል ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ ፡ ማዳበሪያ የሚያመርቱ : የሚያስመጡ ፡ የሚሸጡና የሚያ ሰራጩ ግለሰቦችን ድርጅቶችን የሚያግዙ ፡ የሚያማክሩ ፣ የሚቆ ጣጠሩ መንግሥታዊ አካላትን መሰየም በማስፈለጉ ፡ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመን ግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ክፍል አንድ - ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የማዳበሪያ ማምረትና ንግድ አዋጅ ቁጥር ፩፻፴፯ ህየን፩ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ያንዱ ዋጋ 4 . 40 Iነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ሺ፩ ገጽ ፬፻ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፩ ኅዳር ፲፭ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓም . Federal Negarit Gazeta No . 14 24 November , 1998 – Page 900 ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ፡ “ ማዳበሪያ ” ማለት ለተክሎች ለምግብነት አስፈላጊ | የሆኑትን ንጥረ ነገሮች ለመስጠት አፈር ወይም ተክል ላይ የሚጨመር ካርቦናማ ወይም ካርቦን አልባ የሆነ ሰው ሠራሽ ቁስ ሲሆን ድብልቅን ፣ አካላዊ ድብልቅንና ወደ አንኳርነት የተለወጠ የማዳበሪያ ድብልቅን ይጨምራል ፣ ፍግ ፡ ብስባሽ ፡ አመድ ፣ ጀሶ ፣ ወይም ቆሻሻ በተፈጥሮ ሁኔታቸውና በዚሁ ስማቸው ለንግድ ዓላማ ሲውሉ በዚህ አዋጅ እንደማዳበሪያ ቁስ አይቆጠሩም ፤ “ ነጋዴ ” ማለት በማዳበሪያ ንግድ ላይ የተሰማራ ማንኛውም ሰው ነው ፡ ፫ . “ ሰው ” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው ፣ ፬ . “ ደረጃ ያላሟላ ማዳበሪያ ” ማለት የኢትዮጵያ ደረጃ የጥራት መሥፈርቶችን ያላሟላ ማንኛውም ማዳበሪያ “ የማዳበሪያ ንግድ ሥራ ” ማለት ማዳበሪያ ፣ የማዳበሪያ ድብልቅ ፣ የማዳበሪያ ልዩ ድብልቅ የማስመጣት ፣ በጅምላ የማከፋፈል ፡ የመቸርቸር ፣ የመላክና የማምረት የንግድ ሥራ ነው : ፮ “ የተበከለ ማዳበሪያ ” ማለት በተክሎች ለምግብነት የሚውሉ የንጥረ ነገር ይዘትን ሊያጠፋ ወይም ሊቀንስ የሚችል ማንኛውም ባዕድ ቁስ የተጨመረበትማዳበሪያ “ የተነካካ ከረጢት ” ማለት ስፌቱ ፡ የእርሳስ እሽጋቱ ወይም ሌላ ቦታ ላይ ተፈትቶ ወይም ተቀድዶ እንደገና በነጋዴው ወይም በሌላ ሰው የተሰፋ ማዳበሪያ የያዘ ከረጢት ነው ፣ “ አመዳደብ ” ማለት በማዳበሪያ ውስጥ የሚገኝ በመቶኛ የሚገለጽ የተክል ምግብ ይዘት ነው ፣ “ አምራች ” ማለት ከመጀመሪያው ጥሬ ቁስ ማዳበሪያ | ዎችን የሚያመርት ሰው ነው ፣ “ የማዳበሪያ ድብልቅ ” ማለት የማዳበሪያ አካላዊ ድብልቅና ወደ አንኳርነት የተለወጠ የማዳበሪያ ድብልቅ ነው ፣ ፲፩ . “ የማዳበሪያ አካላዊ ድብልቅ ” ማለት በግዑዝ ወይም ያለግዑዝ ቁስ ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ ማዳበሪያዎችን በአካል በማደባለቅ የሚገኝ የማዳበሪያ ድብልቅ ነው ፣ “ ወደ አንኳርነት የተለወጠ የማዳበሪያ ድብልቅ ” ማለት ማዳበሪያዎችን በሚፈለገው የመጠን ቅንብር በሚገባ በማደባለቅ የሚገኝ የማዳበሪያ ድብልቅ ሲሆን አንድ ላይ ወደ አንኳርነት ሲለወጥ ምንም ዓይነት ኬሚካላዊ አፀግብሮት የማይኖረው ነው ፣ ፲፫ . “ አንኳር ” ማለት የተወሰነ የቅንጣት መጠን ያለው ጠጣር ( ቆቆር ) ማዳበሪያ ማለት ነው ፣ “ የማዳበሪያ ልዩ ድብልቅ ” ማለት ኤጀንሲው መዝግቦ ከያዘው ማዳበሪያ ዓይነት ውጭ ለሙከራ ተግባር የተዘጋጀ ማንኛውም የማዳበሪያ ድብልቅ ነው : “ ውህድ ( ዝንቅ ) ማዳበሪያ ” ማለት ሁለት ወይም ከሁለት በላይ ንጥረ ነገሮችን የያዘ ማዳበሪያ ሲሆን በሚመረትበት ጊዜ ኬሚካላዊ አፀግብሮት የሚኖረው ገጽ ፬፻፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፬ ኅዳር ፲፭ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓም Federal Negarit Gazeta – No . 14 24 November , 1998 – Page 901 ፲ . “ እስመጪ እና ወይም ላኪ ” ማለት ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ የሚያስመጣ እና / ወይም ወደ ውጭ የሚልክ ሰው ነው ፡ ፲፯ . “ ኢንስፔክተር ” ማለት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፳፫ መሠረት የተመደበ የማዳበሪያ ኢንስፔክተር ነው : ፲፰ . “ የኢትዮጵያ ደረጃዎች ” ማለት በኢትዮጵያ ጥራትና ደረጃዎች ባለሥልጣን የተዘጋጁ የማዳበሪያ ደረጃዎች ናቸው ፡ “ የንግድ ፈቃድ ሰጪ ” ማለት እንደአግባቡ የፌዴራል መንግሥት የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ወይም የክልል ወይም ተጠሪነቱ ለፌዴራል መንግሥት የሆነ የከተማ የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ወይም ሌላ አግባብ ያለው የፌዴራል ወይም የክልል አካል ነው ፡ ፳ “ ቦርድ ” ማለት እንደአግባቡ የብሔራዊ ማዳበሪያ ኢንዱስትሪ ኤጀንሲ ወይም የኢትዮጵያ የጥራትና ደረጃዎች ባለሥልጣን ቦርድ ነው ፣ ፳፩ “ ኤጀንሲ ” ማለት የብሔራዊ ማዳበሪያ ኢንዱስትሪ ኤጀንሲ ነው ፡ ፳፪ . “ ባለሥልጣን ” ማለት የኢትዮጵያ የጥራትና ደረጃዎች ባለሥልጣን ነው ። ፫ የአፈጻጸም ወሰን የዚህ አዋጅ ድንጋጌዎች በማዳበሪያ ንግድ ሥራ በተሠማራ ሰው ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ ። ክፍል ሁለት ስለብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት _ ፬• የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አስፈላጊነት ማንኛውም ሰው በማዳበሪያ ንግድ ሥራ ለመሠማራት ከኤጀ ንሲው የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማውጣት ይኖርበታል ፡ ፡ 5 ፭ በማዳበሪያ የንግድ ሥራ ለመሠማራት የሚያበቁ ሁኔታዎች ፩ . ማንኛውም ሰው በማዳበሪያ የንግድ ሥራ ለመሠማራት ኤጀንሲው የሚያወጣቸውን መስፈርቶች አሟልቶ ከኤ ጀንሲው የብቃትማረጋገጫ የምስክር ወረቀትማውጣት ይኖርበታል ። የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እንደተጠበቀ ሆኖ ፡ ሀ ) ማዳበሪያ የሚያመርት የሆነ እንደሆነ በማምረት ሥራ ላይ በቀጥታ የሚሠማሩ የሙያ ብቃትና | ችሎታ ያላቸው ሠራተኞች ያሉት ፡ ለ ) የሚያመርተው ማዳበሪያ ጥራትና የንጥረ ነገር ይዘት ደረጃው የጠበቀ ለመሆኑ ሙከራ ( ፍተሻ የሚያደርግበት ላቦራቶሪ ያለው ፡ መሆን ይኖር በታል ። ፮ ለብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ስለሚቀርብ ማመልከቻ ፩ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፭ መሠረት የብቃት ማረጋገጫ | 6 . Application for Competence Assurance ምስክር ወረቀት ለማግኘት የሚቀርብ ማመልከቻ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀ ቅጽ ላይ ተሞልቶ ለኤጀንሲው መቅረብ አለበት ። የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እንደተጠበቀ ሆኖ ፤ ማዳበሪያ ወይም ድብልቅ ማዳበሪያ አምራች ከሆነ ፡ ሀ ) በማምረት ሥራ ላይ በቀጥታ የሚሠማሩ ባለሙያ ዎችን የሙያ ብቃትና ችሎታ : የሚያመርተው ማዳበሪያ ጥራትና ንጥረ ነገር ይዘት ደረጃውን የጠበቀ ለመሆኑ ሙከራ ፍተሻ የሚያደርግበት ላቦራቶሪ ማቋቋሙን ኤጀንሲው ለዚሁ ተግባር ባዘጋጀው ቅጽ ላይ መሙላት አለበት ። ገጽ ፬፻፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፩ ኅዳር ፲፭ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓ . ም Federal Negarit Gazeta No . 14 24 November , 1998 – Page 902 ፯ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት የሚያስከትሉ ሁኔታዎች | ኤጀንሲው በሚከተሉት ምክንያቶች የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት አይሰጥም ፡ ፩ : ቀደም ብሎ የነበረው የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት የተሰረዘበትና ከተሰረዘበት አንድ ዓመት ያልሞላው ፣ ፪• ይህ አዋጅ ከመውጣቱ በፊት በማዳበሪያ ንግድ ሥራ ጥፋት ፈጽሞ በሌላ ሕግ የተፈረደበትና ቅጣቱን ያልጨረሰ ፣ ፫ . በዚህ አዋጅና በአንቀጽ ፭ የተደነገጉትን ያላሟላ ፣ ፬• ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም በወጣ ደንብ መሠረት የተፈረደ በትና ቅጣቱን ያልጨረሰ ። 1 ፰ ምትክ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ስለማግኘት ፩ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀቱ የጠፋበት ወይም የተበላሸበት ማንኛውም ሰው ለኤጀንሲው በጽሑፍ በማመልከት ምትክ ማግኘት ይችላል ። ፪• ምስክር ወረቀቱ የተበላሸበት ምትክ እንዲሰጠው ሲጠይቅ የተበላሸውን ይመልሳል ። ፫ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት ኤጀንሲው ምስክር ወረቀቱ የጠፋ መሆኑንና ምትክ እንዲሰጥ መጠየቁን የሚገልጽ የጋዜጣ ማስታወቂያ በአመልካቹ ወጪ እንዲወጣ ባደረገ በአንድ ወር ውስጥ ተቃዋሚ አለመቅረቡን በማረጋገጥ በደንቡ የተመለከተውን ክፍያ በማስከፈል ምትክ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ይሰጠዋል ። ፱ . የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ፀንቶ ስለሚቆይበት ጊዜ በዚህ አዋጅ መሠረት የተሠጠ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ለአንድ ዓመት የፀና ይሆናል ። ፲ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት እድሳት ፩ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት የተሰጠው ማንኛውም ሰው ለዚሁ ተግባር የተዘጋጀውን ቅጽ ሞልቶ የምስክር ወረቀቱ የሚያገለግልበት ጊዜ ከማብቃቱ በፊት ባለው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለእድሳት ማመልከቻውን ለኤጀንሲው ማቅረብ አለበት ፤ ፪ : ኤጀንሲው የአመልካቹን ክንውንና ሌሎች አግባብ ያላቸውን ሁኔታዎች ከገመገመ በኋላ ማመልከቻው ከደረሰው በ፲፭ ቀን ውስጥ የአገልግሎት ዋጋ በማስከፈል የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀቱን ያድሣል ። የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ስለማገድ ወይም ስለመ | 11 . Suspension or Cancellation of Certificate of Com ምክንያቶች የብቃት ፩ ኤጀንሲው በሚከተሉት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀትን ሊያግድ ወይም ሊሠርዝ ይችላል ፡ ሀ ) የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀቱን ያገኘው በማታለል ወይም የሀሰት መረጃ ወይም መግለጫ በማቅረብ ከሆነ ፡ ኤጀንሲውን ሳያስፈቅድ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀቱን ለሌላ ሰው ካስተላለፈ ፤ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲ በተደነገገው መሠረት የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀቱን ካላሳደሰ ፤ ማዳበሪያው የኢትዮጵያ የማዳበሪያ ደረጃ የጥራት መስፈርቶችን ያላሟላ ከሆነ ፡ ( ሠ ) የንግድ ፈቃዱ የተሠረዘበት ከሆነ ። ፪ : ኤጀንሲው የብቃትማረጋገጫ ምስክር ወረቀቱን እንደ ሠረዘ የንግድ ፈቃዱም እንዲሠረዝ ለፈቃድ ሰጪው ያሳውቃል ፡ ገጽ ፬፻፫ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፬ ኅዳር ፲፭ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓም Federal NegaritGazeta No . 14 24 November , 1998 – Page 903 ፲፪ መረጃ ስለማቅረብ በማዳበሪያ የንግድ ሥራ የተሠማራ ማንኛውም ሰው ኤጀንሲው መረጃ በሚጠይቅበት ወቅት በተዘጋጀው የመረጃ መሰብሰቢያ ቅጽ ላይ የተጠየቀውን መረጃ ሞልቶ | የማቅረብ ግዴታ አለበት ። ክፍል ሦስት ስለ ማዳበሪያ አመራረት ፤ ንግድ ፤ አያያዝና ሥርጭት ማዳበሪያ ስለማምረት ፡ ወደ ሀገር ውስጥ ስለማስገባት እና | , ስለ ማሰራጨት በሀገርውስጥተመርቶም ሆነ ከውጭ አገር መጥቶየሚከማች የሚሠራጭና ለሽያጭ የሚቀርብ ማንኛውም ማዳበሪያ ፤ ፩ . የኢትዮጵያ ደረጃዎችን ያሟላ ፤ እና ፪ በሀገሪቱ ውስጥ በማዳበሪያነቱ በጥቅም ላይ እንዲውል በኤጀንሲው የተመዘገበ ፥ መሆን አለበት ። ፲፬ ክልከላ ፩ . ማንኛውም ሰው ከኤጀንሲው የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ሳይሰጠውና ከምስክር ወረቀቱ ግዴታ ውጭ ማንኛውንም ማዳበሪያ ማምረት አይችልም ። ፪ . ማንም ሰው በኢትዮጵያ ደረጃ ወይም የኢትዮጵያ ደረጃ በማይገኝበት ጊዜ በኤጀንሲው ያልተወሰነ ማንኛውም ማዳበሪያ ፣ የማዳበሪያ ድብልቅ ወይም ልዩ ድብልቅ በተሰጠው የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ከተወ ሰኑት ዝርዝሮች ጋር በማይስማማ ሁኔታ ከውጭ ማስገባት ፣ ለሽያጭ ማምረት ወይም መሽጥ ፣ ለሽያጭ ማቅረብ ወይም ለሽያጭ ማሳየት ወይም ማከፋፈል አይችልም ። ፫ . ማንም ሰው የሚከተሉትን መሽጥ ፤ ለሽያጭ ማቅረብ ፤ ወይም ለሽያጭ ማሳየት ወይም ማከፋፈል አይችልም ፤ ሀ ) ሌላ ማዳበሪያ የሚሰጥበትን ስም በማስመሰል ወይም በመተካት የተዘጋጀማንኛውምማዳበሪያ ፤ የተበከለማንኛውም ማዳበሪያ ፤ ሐ ) የሀሰት ወይም የሌላውን ግል ድርጅት ወይም ኩባንያ ማዳበሪያ የሚያመርት በማስመሰል ምልክቱ ወይም መያዣው ይህንኑ የሐሰት ወይም የሌላ ድርጅት ወይም ኩባንያ ስም የያዘ ማንኛውም ማዳበሪያ ፤ ምልክቱ ወይም መያዣውን በሐሰት የራስ በማስ መሰል አሳሳች መረጃ የሚሰጥ ማንኛውንም ማዳበሪያ ። ፬ ማንኛውም ሰው የተፈጥሮ ማዳበሪያ ከውጭ ወደ ሀገር - ውስጥ ማስገባት አይችልም ። ፲፭ ስለማዳበሪያ ማሸጊያ ፡ ስለአስተሻሸግና ምልክት አደራረግ | 15 . Package , Packing and Labeling of Fertilizer ፩ የማዳበሪያ ማሽጊያ ከረጢት ስሪትና በከረጢቱ ላይ መደረግ ያለባቸው ምልክቶች የኢትዮጵያ ያስተሻሽግና ምልክት አደራረግ ደረጃን ያሟሉ መሆን አለባቸው ። በኢትዮጵያ ደረጃ ማሸጊያ ከተደነገገለት ውጪ የሆነ የማዳበሪያ ዓይነት ከውጪ ሀገር ሲመጣ ወይም ከሀገር ሲመረት መያዣው ፕላስቲክ ወይም ጣሳ ከሆነ ማሸጊያው ተፈላጊውን መረጃ የያዘ መሆን አለበት ። ፲፮• በከረጢት ያልታሸገ ማዳበሪያ ስለመሽጥ የዚህ አዋጅ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ፩ . የማዳበሪያ ችርቻሮ ነጋዴ በማንኛውም ሰዓት ከእያን ዳንዱ የማዳበሪያ ዓይነት አንዳንድ ከረጢት ያልታሸገ ማዳበሪያ ለሽያጭ ሊይዝ ይችላል ። ገጽ ፬፻፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፬ ኅዳር ፲፭ ቀን ፲፱፻፶፩ ዓም Federal Negarit Gazeta No . 14 24 November , 1998 - - Page 904 ፪• ማንኛውም ማዳበሪያ አምራችና አስመጪ ለድብልቅ ፤ ለልዩ ድብልቅና ለውህድ ( ዝንቅ ) ማዳበሪያ አምራችና ለሰፋፊ እርሻዎች ብቻ ያልታሸገ ማዳበሪያ ሊሸጥ ይችላል ። ፲፯ ደረጃ ያላሟላ ማዳበሪያ ስለመሸጥ ፩ . የዚህ አዋጅ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው | 17 . Selling of sub - Standard Fertilizer ማንኛውም ሰው ማንኛውንም ያልተበከለ ነገር ግን ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ዝቅ ያለ ማዳበሪያ በሚከተሉት ሁኔታዎች መሸጥ ፣ ለሽያጭ ማቅረብ ፣ ማከማቸት ፣ ለሽያጭ ማሳየት ወይም ማከፋፈል ይችላል ፤ ሀ ) ደረጃ ባላሟላው ማዳበሪያ ከረጢት ላይ በቀይ ቀለም በጉልህ የኢትዮጵያ ደረጃ ያላሟላ የሚሉ ቃላትና X ምልክት የተደረገ እንደሆነ ፤ ለ ) ደረጃ ያላሟላ ማዳበሪያ የሚሸጠው ለድብልቅ ወይም ልዩ ድብልቅ ማዳበሪያ አምራቾች ፣ ለእርሻ ምርምር ተግባር ፣ ለግብርና ቢሮዎች ፣ ለእርሻ ምርምር ተቋማት ፡ ለዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆች ብቻ የሆነ እንደሆነ እና ፤ ሐ ) ደረጃውን ያላሟላማዳበሪያ ለመሸጥ ከኤጀንሲው አስቀድሞ ፈቃድ የተገኘ እንደሆነ ። ፪ : ኤጀንሲው ደረጃ ያላሟሉ ማዳበሪያ የፍተሻ ውጤት ሲደርሰው በንጥረ ነገሩ ይዘት መጠን የመሸጫ ዋጋውን ይወስናል ። ፲፰ የተበከለ ማዳበሪያን ስለማስወገድ ማንኛውም ማዳበሪያ የተበከለ መሆኑ ከተረጋገጠ ኤጀንሲው በሚያወጣው መመሪያ መሠረት በጥቅም ላይ እንዳይውል ይወገዳል ። = ፲፱• የማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጭት ፩ . ማንኛውም አስመጪ ማዳበሪያ የሚገዛበትን ፤ ወደብ | , ላይ የሚያደርስበትንና ከወደብ በማንሳት የሚያጓጉዝ በትን የጊዜ ሰሌዳ ለኤጀንሲው የማሳወቅ ግዴታ ለበት ። ፪ . ማንኛውም አስመጪ ያስመጣውን ማዳበሪያ በሰጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ከወደብ ወደ መሀል አገር ማጓጓዝ አለበት ። ፫ . ማንኛውም አስመጪ ፣ የጅምላና ችርቻሮ ነጋዴ የያዘውን ማዳበሪያ ለተጠቃሚ በሚፈለገው ወቅትና | ቦታ ለሽያጭ ማቅረብ አለበት ። ስለፈቃድ አሰጣጥ ፩ ማዳበሪያ ለማምረት ፡ ለማስመጣት ፣ በጅምላና | 20 . Licensing በችርቻሮ ለመነገድማመልከቻ ለፈቃድ ሰጪው ሲቀር ብለት አመላካቹ ከኤጀንሲው የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት የተሰጠው ለመሆኑ ፈቃድ ሰጪው ማረጋገጥ አለበት ። ፪• የምርምር ተቋማት ምርምር ለማካሄድና በግብርና ሥራ ላይ የተሰማሩ ኢንቨስተሮች በራሳቸው እርሻ ላይ ለራሳቸው አዳዲስ የማዳበሪያ ዓይነቶችን ለማስገባት ሲፈልጉ ከኤጀንሲው ፈቃድ ማግኘትና ስለአገባባቸው ኤጀንሲው ያወጣውን መመሪያ መከተል አለባቸው ። ፫ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) መሠረት ፈቃድ ያገኘበትን ማዳበሪያ ለሌላ ማንኛውም ሰው አሳልፎ መስጠት ወይም መሸጥ አይችልም ። ገጽ ፬፻፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፬ ኅዳር ፲፭ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓም Federal Negarit Gazeta No . 14 24 November , 1998 – Page 905 ክፍል አራት አስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶችና የሥራ ድርሻቸው 3 ፳፩ የባለሥልጣኑ ተግባርና ሃላፊነት ባለሥልጣኑ በመቋቋሚያ ሕጉ የተሰጡት ሥልጣንና ተግባር እንደተጠበቁ ሆኖ ፡ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባር ይኖሩታል ፡ ፩ ከኤጀንሲው በሚቀርብለት የተፈላጊማዳበሪያ ዓይነት ዝርዝር መሠረት ከውጪ የሚገቡ ማዳበሪያዎችን ይመረምራል ፤ ጥራታቸውን ያረጋግጣል ፣ ፪ . የዚህ አዋጅ አንቀጽ ( ፳፪ ) እንደተጠበቀ ሆኖ ፤ የሀገር | ውስጥ ማዳበሪያ አምራቾች የሚያመርቱት ማዳበሪያ የጥራት ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን ያረጋግጣል ። ፳፪ የኤጀንሲው ተግባርና ሃላፊነት ኤጀንሲው በማቋቋሚያ ሕጉ የተሰጠው ሥልጣንና ተግባር | 22 Duties and Responsibilities of the Agency እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ ፩ ወደሀገር ውስጥ የሚገቡትንም ሆነ በሀገር ውስጥ የሚመረቱትን የማዳበሪያ ዓይነቶች ይወስናል ፤ ፪ የማዳበሪያ ዓይነቶች በህዝብ ማስታወቂያ እንዲወጡ ያደርጋል ፤ ይከታተላል ፤ ይቆጣጠራል ፣ ዝርዝራቸ ውንም በየጊዜው ለባለሥልጣኑ ይገልጸል ፤ ማዳበሪያ ማምረት ፣ ማደባለቅ ፤ ማስመጣት ፤ በጅምላና በችርቻሮ መሸጥን በተመለከተ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል ፤ ያድሳል ፣ ያግዳል ፤ ይሰርዛል ፤ ፬ ይህን አዋጅ ለማስፈጸም የኢንስፔክሽን ቡድን አቋቁሞ ኢንስፔክተሮችን ይመድባል ፤ ላቦራቶሪዎችን ያቋቁማል ፤ ያደራጃል ፣ ያስተዳድራል ፤ የማዳበሪያ ጥራትን ይመረምራል ፤ ይቆጣጠራል ፤ ፭ ዋጋን ለማረጋጋት ስልት ይቀይሳል ፤ ተግባራዊነቱን ይከታተላል ፤ ይቆጣጠራል ፤ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገ ኘውም መወሰድ ስለሚገባቸው እርምጃዎች አጥንቶ ለመንግሥት ሀሳብ ያቀርባል ፤ ሲወሰንም ተግባራዊ ነቱን ይከታተላል ፣ ማዳበሪያ ለየሰብል ዘመኑ በሀገሪቱ ውስጥ በበቂ መጠን መቅረቡንና ወደ ክልሎች በወቅቱ መሠራጨቱን ይከታተላል ፤ ይቆጣጠራል ፤ ይህን አዋጅ ለማስፈጸም ሥልጣኑን በውክልና ለመስ ጠትና ውክልናውተፈጻሚየሚሆንባቸውን ሁኔታዎች ለመወሰን ይችላል ፣ ቿ ማዳበሪያ እንዳይሸጥ ሲታገድ በላቦራቶር ምርመራ ውጤት ላይ በመመርኮዝ ውሳኔ ይሰጣል ፤ ፳፫ የኢንስፔክተር ተግባርና ሃላፊነት ኢንስፔክተሩ በኤጀንሲው የሚመደብ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ሃላፊነት ይኖሩታል ፤ ፩ በማምረት ፣ በክምችት በሽያጭ ላይ ወይም በማን ኛውም ሁኔታ ስለሚገኝ ማንኛውንም አምራች ፣ አስመጪ ፣ ጅምላ ነጋዴ ፣ ወይምችርቻሮ ነጋዴ መረጃ ይጠይቃል ፤ አግባብ ባላቸው የኢትዮጵያ ደረጃዎች በተገለጸው መሠረት የማዳበሪያ ናሙናዎች ይወስዳል ፤ በሦስት ቅጅ የናሙና አወሳሰድ ዝርዝር አዘጋጅቶ ከእያንዳንዱ ቅጅ ጋር የታሸጉና ልዩ ምልክት የተደረገባቸው ናሙናዎች በማቀናጀት አንድ ቅጅ ለነጋዴው ፣ አንድ ቅጅ ለላብራቷር ምርመራ ፡ ሦስተኛውን ቅጂ ከሱ ቀጥሎ ላለው ከፍተኛ ባለሥልጣን ያቀርባል ፤ ገጽ ፬፻፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፬ ኅዳር ፲፭ ቀን ፲፱፻፶፩ ዓም Federal Negarit Gazeta No . 14 242 November , 1998 – Page 906 ፫• ማንኛውም ማዳበሪያ በዚህ አዋጅ ድንጋጌ መሠረት በትክክል መመረቱን ወይም በመመረት ላይ መሆኑን ፤ መሸጡን ፤ ለሽያጭ መቅረቡን ፤ መከማቸቱን ፤ ለሽያጭ መታየቱን ወይም መከፋፈሉን ለማረጋገጥ በቦታው ተገኝቶ ይፈትሻል ፣ የማንኛውም ማዳበሪያ ሥራ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) የተዘረዘሩትን ሥራዎች በሚጥስ ሁኔታ መከናወኑን ፣ እየተከናወነ መሆኑን ወይም ሊከናወን መታቀዱን የሚያሳምን ምክንያት ካጋጠመው ማዳበ ሪያውእንዳይሸጥ ማገድ ይችላል ፣ ፭ ኢንስፔክተሩበዚህ አንቀጽንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት ላገደው ማዳበሪያ በጽሁፍ የሽያጭ ማገጃ ማስታወቂያ ሰጥቶ የእገዳውን ምርመራ ውጤት ለኤጀንሲው ያሳውቃል ፤ ፮ ማንኛውም የማዳበሪያ አምራች ፤ አስመጪ ፤ የጅምላና የችርቻሮነጋዴ በእጁየሚገኘውን ማዳበሪያ አለአግባብ በማከማቸት ሰው ሰራሽ እጥረት እንዳይፈጠር ይከታ ተላል ፣ ይቆጣጠራል ። ክፍል አምስት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፬• የመተባበር ግዴታ በዚህ አዋጅ መሠረት ኢንስፔክተሩ ተግባሩን ማከናወን | እንዲችል የሚመለከተው ማንኛውም ሰው የመተባበር | bound to afford all necessary facilities to him for the ግዴታ አለበት ። ስለ አቤቱታ አቀራረብ በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወስዳቸው እርምጃዎች ቅር | 25 . Appeal የተሰኘ ማንኛውም ሰው ፤ ፩ የኤጀንሲውን የሥራ ድርሻ በተመለከተ ለኤጀንሲው የሥራ አመራር ቦርድ ፤ ፪ . የባለሥልጣኑን የሥራ ድርሻ በተመለከተ ለባለሥ ልጣኑ የሥራ አመራር ቦርድ ፣ አቤቱታ ማቅረብ ይችላል ። ፳፮ : ስለ ቅጣት ፩• ሆን ብሎ የተበከለ ማዳበሪያ ወይም ያልተመዘገበ | 26 . Penalties ማዳበሪያ ለሽያጭ ያቀረበ ወይም የሸጠ ማንኛውም ሰው ከ፰ ዓመት ባላነሰና ከ7 ዓመት ባልበለጠ የእሥራት ቅጣትና ከብር፳፭ ሺህ በማያንስና ከብር ፴፬ ሺህ ባልበለጠ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ። ምንም ፪ . በዚህ አዋጅ በአንቀጽ ፲፯ ከተደነገገው ውጭ የኢትዮ ጵያን ደረጃዎች ያላሟላ ማዳበሪያ ለሽያጭ ያቀረበ ወይም የሸጠ ማንኛውም ሰው ከ፭ ዓመት ባላነሰና ከሲ ዓመት ባልበለጠ የእሥራት ቅጣትና ከብር ፳፭ ሺህ ባላነሰና ከብር ፶ ሺህ ባልበለጠ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ። ፫ የከረጢት ስሪት ደረጃውን ያልጠበቀ መሆኑን እያወቀ በተጠቀሰው ከረጢት ማዳበሪያን ለሽያጭ ያቀረበ | ወይም የሸጠ ማንኛውም ሰው ከ፫ ዓመት ባላነሰና ከ፭ ዓመት ባልበለጠ የእሥራት ቅጣትና ከብር ፲፭ ሺህ በማያንስና ከብር ከ፳፭ ሺህ በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ። በከረጢቱ ላይ የምልክት አደራረጉና የከረጢቱ አስተ ሻሽግ ደረጃውን ያልጠበቀ ፤ በከረጢቱ ውስጥ ያለው የማዳበሪያ ክብደት መጠን ከተከፈለበት ዋጋ ያነሰ ማዳበሪያ ሆን ብሎ ለሽያጭ ያቀረበ ወይም የሸጠ ማንኛውም ሰው ከ፩ ዓመት ባላነሰና ከ፫ ዓመት ባልበለጠ የእሥራት ቅጣትና ከብር ፭ ሺህ ባላነስና ከብር ፲፭ ሺህ ባልበለጠ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ። ገጽ ፬፻፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፬ ኅዳር ፲፭ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓም Federal Negarit Gazeta No . 14 24ሥNovember , 1998 – Page 907 ፭ የኤጀንሲው ኢንሰፔክተር ወይም ሠራተኛ በዚህ | አዋጅ መሠረት ሥልጣንና ተግባሩን ለመወጣት ማስረጃ ሲጠይቅ ለመተባበር ፈቃደኛ ያልሆነ ማንኛውም ሰው ከ፩ ዓመት በማይበልጥ የእሥራት ቅጣትና ከብር ፭ ሺህ ባላነሰና ከብር ፲ ሺህ ባልበለጠ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ። ኢንስፔክተሩን ያሳሳተ ወይም ያታለለ ፡ የተወሰደ ናሙና ወይም ለምርመራ የተሰጠ ናሙና በትክክል ምርቱን እንዳይወክል ሆን ብሎ ያዛባ ማንኛውም ሰው ከ፩ ዓመት ባላነሰና ከ፫ ዓመት ባልበለጠ የእሥራት ቅጣትና ከብር ፲ ሺህ ባላነሰና ከብር ፲፭ ሺህ ባልበለጠ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ። ፯ ሆን ብሎ የታሸገ መጋዘን የከፈተማንኛውም ሰውእስከ ፩ ዓመት በሚደርስ የእሥራት ቅጣት ወይም ከብር ፭ ሺህ ባላነሰና ከብር ፲ ሺህ ባልበለጠ የገንዘብ መቀጮ | ይቀጣል ። - ፳፯ ደንብ የማውጣት ሥልጣን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ይህን አዋጅ ለማስፈጸም ደንብ | ሊያወጣ ይችላል ። ፳፰ መመሪያዎች ኤጀንሲው ይህን አዋጅ ተግባራዊ ለማድረግ የሚረዱ | መመሪያዎችን ሊያወጣ ይችላል ። የሌሎች ሕጐች ተፈጻሚነት ፩ . የኢንቨስትመንት እንዲሁም የንግድ ምዝገባና ቁጥጥር | ሕጐች በማዳበሪያ ንግድ ሥራ በተሠማራ ሰው ላይ እንደ አግባቡ ተፈጻሚ ይሆናሉ ። ፪• ማንኛውም ሌላ ሕግ ወይም የተለመደ አሠራር ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረን ሆኖ ካልተገኘ በቀር በዚህ አዋጅ በተመለከቱት ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት ይኖረዋል ። ፬ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅከኅዳር ፲፭ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። | አዲስ አበባ ፡ ኅዳር ፲፭ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓም• ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት