×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
በበረራ ደህንነት ላይ ስለሚፈጸሙ ወንጀሎች የወጣ አዋጅ ቁጥር ፴፩/፲፱፻፹፰

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሁለተኛ ዓመት ቁጥር ፲፱ አዲስ አበባ የካቲት ፲፬ ቀን ፲፱፻ዥ፰ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅቁጥር ፴፩ / ፲፱፻ዥ፰ ዓም : በበረራ ደህንነት ላይ ስለሚፈጸሙ ወንጀሎች የወጣ አዋጅ . . . . . ገጽ ፻፳፬ አዋጅቁጥር ፴፩ / ፲፱፻፳፰ በበረራ ደህንነት ላይ ስለሚፈጸሙ ወንጀሎች የወጣ አዋጅ በበረራ ደህንነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች አስጊና የሰው | ሕይወትና ንብረት በከፍተኛ አደጋ ላይ የሚጥሉ መሆናቸውን | aviation greatlyendangerlife and property , international conven በመገንዘብ እነዚህኑ ሕገ ወጥ ድርጊቶች ለመቋቋም ዓለምአቀፍ ስምምነቶች የወጡና ኢትዮጵያ ስምምነቶቹን ከፈረሙ አገሮች አንዷ በመሆኗ ፤ ኢትዮጵያ ያጸደቀቻቸውን ዓለምአቀፍ ስምምነቶች ወደ ተግባር ለመተርጎም የኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ አካል የሆነ ሕግ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ በበረራ ደህንነት ላይ ስለሚፈጸሙ ወንጀሎች የወጣ አዋጅቁጥር ፴፩ / ፲፱፻ዥ፰ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ በዚህ አዋጅ ውስጥ ፤ ፩ “ በበረራላይ ያለ አይሮፕላን ” ማለት የአይሮፕላኑ የውጭ በሮች ከተዘጉበት ጊዜ ጀምሮ በሩ እስከሚከፈት ድረስ ያለውን ጊዜ የሚመለከት ሲሆን አይሮፕላኑ ተገዶ ያረፈ እንደሆነ ይህ ጊዜ አይሮፕላኑንና በውስጡ ያሉትን ሰዎችናንብረቱን ሙሉ በሙሉለማስለቀቅየሚወስደውን ጊዜ ይጨምራል ፤ ያንዱ ዋጋ 160 ነጋሪት ጋዜጣፖሣቁ ቸሺ፩ ገጽ ፻፲፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፱ የካቲት ፲፬ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ . ም . Federal Negarit Gazeta No . 19 22 February 1996 Page 165 ፪ . “ በአገልግሎት ላይ ያለ አይሮፕላን ” ማለት የአየር ትራንስፖርት ወይም የአይሮፕላን ሠራተኞች ለተወሰነ በረራ ከሚያደርጉት ቅድመ ዝግጅት ጀምሮ አይሮፕላኑ ካረፈ በኋላ እስከ ፳፬ ሰዓት ድረስ ያለውን ጊዜ የሚመ ለከት ሲሆን ፡ በማናቸውም ሁኔታ ከዚህ በላይ በንዑስ ኣንቀጽ ( ፩ ) በበረራ ላይ ያለ አይሮፕላን ከሚሸፍነው ጊዜ ያነሰ አይሆንም ። ፫ አይሮፕላን ስለመጥለፍ ማንም ሰው ሆን ብሎ ከሕግ ውጭ በኃይል ሥራ ፡ በዛቻ ወይም በሌላ በማንኛውም የማስፈራሪያ ዘዴ በአገልግሎት ላይ ያለ | አይሮፕላንን የያዘ ወይም በቁጥጥር ሥር ያዋለ እንደሆነ ከ፲፭ እስከ ፳፭ ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል ። ፬ በበረራ ላይ ያለን አይሮፕላን አስጊ ሁኔታ ላይ ስለመጣል ፩ ማንም ሰው በቸልተኝነት በበረራ ላይ ባለ ኣይሮፕላን ውስጥ በሰው ላይ የኃይል ሥራ ከፈጸመና ድርጊቱ የአይሮፕላኑን ደህንነት አስጊ ሁኔታ ላይ የሚጥል የሆነ እንደሆነ ከ፭ እስከ ፲፭ ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል ። ፪ . ማንም ሰው ሆን ብሎ በበረራ ላይ ባለ አይሮፕላን ውስጥ በሰው ላይ የኃይል ሥራ ከፈጸመና ድርጊቱ የአይሮፕላኑን ደህንነት አስጊ ሁኔታ ላይ የሚጥል የሆነ እንደሆነ ከ፲፭ እስከ ፳፭ ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል ። ፭ በአገልግሎት ላይ ባለ ኣይሮፕላን ላይ አደጋ ስለማድረስ ፩ . ማንም ሰው በቸልተኝነት በአገልግሎት ላይ ያለን ኣይሮ ፕላን ያወደመ ፡ ለበረራ ብቁ እንዳይሆን ያደረገ ወይም የበረራ ላይ ደህንነቱ ለአደጋ እንዲጋለጥ ለማድረግ የሚችል ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ ከ፭ እስከ ፲፭ ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይቀጣል ። ፪ . ማንም ሰው ሆን ብሎ በአገልግሎት ላይ ያለን አይሮፕላን | ያወደመ ፡ ለበረራ ብቁ እንዳይሆን ያደረገ ወይም የበረራ | ላይ ደህንነቱን ለአደጋ እንዲጋለጥ ለማድረግ የሚችል | ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ ከ፲፭ እስከ ፳፭ ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል ። ፮ በአገልግሎት ላይ ባለ አይሮፕላን ውስጥ አደጋ የሚያደርስ መሣሪያ ወይም ዕቃ ስለማስቀመጥ ማንም ሰው በቸልተኝነት በአገልግሎት ላይ የሚገኝን አይሮፕላን ለማውደም ወይም ለበረራ ብቁ እንዳይሆን ወይም የበረራ ደህንነቱን ለአደጋ እንዲጋለጥ ለማድረግ የሚችል መሣሪያ ወይም ዕቃ በማናቸውም ዘዴ በአይሮ ፕላኑ ውስጥ ያስቀመጠ ወይም እንዲቀመጥ ያስደረገ የሆነ እንደሆነ ከ፭ እስከ ፲፭ ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይቀጣል ። ፪ ማንም ሰው ሆን ብሎ በኣገልግሎት ላይ የሚገኝን አይሮፕላን ለማውደም ወይም ለበረራ ብቁ እንዳይሆን ወይም የበረራ ደህንነቱን ለአደጋ እንዲጋለጥ ለማድረግ የሚችል መሣሪያ ወይም ዕቃ በማናቸውም ዘዴ በአይሮ ፕላኑ ውስጥ ያስቀመጠ ወይም እንዲቀመጥ ያስደረገ የሆነ እንደሆነ ከ፲፭ እስከ ፳፭ ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይቀጣል ። ፯• ለበረራደህንነት የሚያገለግሉ ተቋሞችን ወይም መሣሪያዎችን ስለማሰናከል ፩ . ማንም ሰው በቸልተኝነት ለበረራ ደህንነት የሚያገለግሉ ተቋሞችን ወይም መሣሪያዎችን ያወደመ ፡ ያበላሸ ወይም አሰራራቸውን ለማሰናከል ጣልቃ የገባእንደሆነናድርጊቱ በበረራ ላይ የሚገኝን አይሮፕላን ለአደጋ የሚያጋልጥ የሆነ እንደሆነ ከ፭ እስከ ፲፭ ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይቀጣል ። ገጽ ፻፰፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፬ የካቲት ፲፬ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ . ም . Federal Negarit Gazeta No . 19 22 February 1996 Page 166 ፪ . ማንም ሰው ሆን ብሎ ለበረራ ደህንነት የሚያገለግሉ ተቋሞችን ወይም መሣሪያዎችን ያወደመ ፡ ያበላሸ ወይም አሰራራቸውን ለማሰናከል ጣልቃ የገባ እንደሆነናድርጊቱ በበረራ ላይ የሚገኝን አይሮፕላን ለአደጋ የሚያጋልጥ የሆነ እንደሆነ ከ፲፭ እስከ ፳፭ ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይቀጣል ። ፰• የበረራ ደህንነትን ለአደጋ ስለሚያጋልጥ ሀሰተኛ መረጃ ፩ . ማንም ሰው በቸልተኝነት በበረራ ላይ የሚገኝን አይሮ ፕላን ለአደጋ የሚያጋልጥ ሀሰተኛ መረጃ ያስተላለፈ የሆነ እንደሆነ ከ፭ እስከ ፲፭ ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይቀጣል ። ፪ : ማንም ሰው ሆን ብሎ በበረራ ላይ የሚገኝን አይሮፕላን ለአደጋ የሚያጋልጥ ሀሰተኛ መረጃ ያስተላለፈ የሆነ አንደሆነ ከ፲፭ እስከ ፳፭ ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይቀጣል ። ፱ ከባድ ሁኔታ ከላይ የተዘረዘሩት ወንጀሎች በተፈጸሙ ጊዜ በሕይወት ፡ በአካል ወይም በጤና ላይ ጉዳት የደረሰ እንደሆነ እንደጥፋቱ ክብደትቅጣቱ የዕድሜ ልክ ጽኑእስራት ወይም ሞት ይሆናል ። ፲ . የሥራ ግዴታን ስለመጣስ በበረራ ደህንነት ላይ ሊፈጸም የሚችለውን ማንኛውንም ወንጀል ለመከላከል ወይም ለመቆጣጠር ኃላፊነት የተጣለበት ሠራተኛ የሥራ ግዴታውን በአግባቡ ሳይወጣ ቀርቶ በበረራ | ላይ ወይም በአገልግሎት ላይ ባለ አይሮፕላን ወይም ለበረራ ደህንነት በሚያገለግሉ መሣሪያዎች ወይም ተቋሞች ላይ አደጋ ሊያደርስ የሚችል መሣሪያ ወይም ዕቃ ተቀምጦ ቢገኝ ከ፭ እስከ ፲፭ ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል ፤ ድርጊቱ በሕይወት ፥ በአካል ወይም በጤና ላይ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ ቅጣቱ እስከ ፳፭ ዓመት ጽኑ እስራት ሊደርስ ይችላል ። ፲፩ አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከየካቲት ፲፬ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። ኣዲስ ኣበባ የካቲት ፲፬ ቀን ፲፱፻T፰ ዓም ዶ ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?