×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 20959

      Sorry, pritning is not allowed


የሰበር መ / ቁ . 20959
ቀን ሠኔ 09/1998 ዓ.ም.
ዳኞች፡- 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
2. አቶ አብዱልቃድር መሐመድ
3. አቶ ጌታቸው ምህረቱ
4. አቶ መስፍን ዕቁበዮናስ
5. ወ / ት ሂሩት መለሰ
አመልካች፡- የአንበሣ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት
እነ ፍቃዱ ሸሪካ / 31 ሠዎች /
ፍ ር ድ
በዚህ ጉዳይ ለሰበር ችሎት የቀረበው ክርክር ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠርኩ / ን /
ይወስንልኝ / ን / የሚል ዳኝነት በመጠየቅ የሚቀርብ ክስ የክስ ምክንያት / Cause of
action / አለው ? ወይስ የለውም ? የሚለውን የህግ ነጥብ የሚመለከት ነው ፡፡
የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ መ / ሰጭ ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠርኩ / ን /
ይወሰንልኝ / ን / በማለት ያቀረቡትን ክስ በመቀበል አከራክሮ ውሣኔ ሰጥቷል ፡፡ በውሣኔው
ላይ ይግባኝ የቀረበለት ይግባኝ ሰሚው ፍ / ቤትም ከላይ የተመለከተውን የህግ ነጥብ
ሳይመረመር አልፎታል ፡፡
አመልካች በዚህ ችሎት ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ጉዳዩ ለሰበር
ችሎት እንዲቀርብ በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት መ /
ሰጭ መልስ ሰጥቷል ።
ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ግልባጭ
ማ 1 ፈጽሟል ፡፡
ችሎቱም ላልተወሰነ
ጊዜ እንደተቀጠርኩ / ን / ይወሰንልኝ / ን / የሚል ዳኝነት
በመጠየቅ የሚቀርብ ክስ የክስ ምክንያት / cause of action / አለው ? ወይስ የለውም ?
የሚለውን የህግ ነጥብ መሰረት በማድረግ አቤቱታ ያቀረበበትን ውሣኔ መርምሯል ።
ይህ ችሎት ሰመ.ቁ. 16273 ጥቅምት 22 ቀን 1998 በሰጠው ውሣኔ አግባብነት
ያላቸውን የህጉን ድንጋጌዎች በመተርጎም አንድ ሠራተኛ ከውሉና ከአሰሪና ሠራተኛ
ሕጉ አንፃር ሊያገኘው የሚገባና የቀረበለት ጥቅም ካላ የቀረበት ጥቅም እንዲሰጠው
መጠየቅ / ክስ ማቅረብ / የሚችል ሲሆን ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠርኩ ይወሰንልኝ ብቻ
የሚቀርብን ክስ የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድም ሆነ የሥራ ክርክር ችሎት
ተቀብለው ሊያዩ የሚችሉበት የሕግ ምክንያት የለም በማለት የሕግ ትርጉም ሰጥቷል ፡፡
በዚህ ጉዳይም የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ መ /
ሰጭ ያቀረቡትን
ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠርኩ / ን / ይወስንልኝ / ን / በማለት ያቀረቡትን ክስ የክስ ምክንያት
የለውም በማለት
የነበረበት ሲሆን ጉዳዩን ተቀብሎ በማከራከር ውሣኔ
በመስጠቱ መሠረታዊ የሕግ
ው ሣ ኔ
የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ በመቁ . 151/01/97 የሰጠው ውሣኔና
የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት በመቁ . 39562 የሰጠው ትዕዛዝ / ውሣኔ /
ተሽሯል ፡፡
ግራ ቀኙ በዚህ ችሎት ያወጡትን ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻሉ ፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል ፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ፡፡
ፈዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ግልባጭ
ቀን - July

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?