የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሁለተኛ ዓመት ቁጥር ፳፩ አዲስ አበባ ሚያዚያ ፲፯ ቀን ፲፱፻፳፰ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፴፫ / ፲፱፻፳፰ ዓ . ም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት | ( ማሻሻያ ) አዋጅ . . . . . . . . . . . . . . ገጽ ፻፰፱ አዋጅ ቁጥር ፴፫ / ፲፱፻፳፰ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት አዋጅን ለማሻሻል የወጣ አዋጅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት | አዋጅን ማሻሻል በማስፈለጉ ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ | tion ; መንግሥት አንቀጽ ፵፱ ( ፪ ) እና ፲፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት ( ማሻሻያ ) አዋጅ ቁጥር ፴፫ / ፲፱፻፳፰ ” ተብሎ ሊጠቀስ | ይችላል ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር ፲፬ / ፲፱፻፳፰ እንደሚከተለው ተሻሽሏል ፤ ፩ . በአንቀጽ ፪ ስር የሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፭ ) | ተጨምሯል ፤ “ ፤ “ የቴክኒክ እርምት ” ማለት የቋንቋና የሌላም ዓይነት ግድፈት ማስተካከያ ሲሆን በማናቸውም ረገድ የሕጉን ይዘት የማይለውጥማሻሻያ ነው ። ” ፪ . በአንቀጽ ፰ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) መጨረሻ ላይ “ ሆኖም ሕጉ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከመውጣቱ በፊት የቴክኒክ እርምት ማድረግ የሚያስፈልግ ሆኖ ሲገኝ ጉዳዩ ለምክር ቤቱ ቀርቦ እርምቱ ይደረጋል ” የሚል ሐረግ ተጨምሯል ። ያንዱ ዋጋ ) | ነጋሪት ጋዜጣ ፖ . ሣቁ• Tሺ፩ ገጽ ፻፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፩ ሚያዚያ ፲፯ ቀን ፲፱፻ዥ፰ ዓም : Federal Negarit Gazeta No . 21 25 April 1996 Page 170 ፫ ከአንቀጽ ፰ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) ቀጥሎ የሚከተሉት አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) እና ( ፱ ) ተጨምረዋል ፤ ሀ ) “ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) መሠረት የቴክኒክ እርምት ሲደረግ ፕሬዚዳንቱ በአፈ ጉባኤው አማካኝነት እንዲያውቁት ይደረጋል ። ” ለ ) “ ፬ ፕሬዚዳንቱ ተቃውሞ ያላቸው እንደሆነ የተደ ረገው የቴክኒክ እርምት ቀርቶ በጉዳዩ ላይ የሕግ ረቂቅ ለምክር ቤቱ ይቀርባል ። ” ፩ . የአንቀጽ ፰ የቀድሞው ንዑስ አንቀጽ ፪ ) ንዑስ አንቀጽ ( ፭ ) ሆኖ ይነበባል ። ፫ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከሚያዚያ ፲፯ ቀን ፲፱፻ዥ፰ ዓ . ም . ጀምሮ የጸና [ 3 . Effective Date ይሆናል ። አዲስ አበባ ሚያዚያ ፲፯ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ