×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር 247,93 የነዳጅ ዋጋ ማረጋጊያ ፈንድ ማቋቋሚያ አዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሰባተኛ ዓመት ቁጥር ፴፯ አዲስ አበባ ሰኔ ፳፮ ቀን ፲፱፻ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፵፯ ፲፱፻፫ ዓ.ም የነዳጅ ዋጋ ማረጋጊያ ፈንድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፪፻፵፯ ፲፱፻፲፫ የነዳጅ ዋጋ ማረጋጊያ ፈንድ ለማቋቋም የወጣ አዋጅ የነዳጅ ምርቶች ከማንኛውም ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ እንቅ ስቃሴ ጋር ያላቸውን ከፍተኛ ትስስር እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ | fuel products have with every economic and social activity በመገንዘብ ፣ የነዳጅ ዋጋን ማረጋጋት የሚያስችል ፈንድ ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የነዳጅ ዋጋ ማረጋጊያ ፈንድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፪፻፵፯ ፲፱፻፳፫ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። መ ቋ ቋ ም የነዳጅ ዋጋ ማረጋጊያ ፈንድ ( ከዚህ በኋላ “ ፈንዱ ” እየተባለ የሚጠራ ) የገንዘብ ሚኒስቴር በሚከፍተው ልዩ የባንክ ሂሣብ ውስጥ ተቀማጭ እንዲሆን በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። የፈንዱ ዓላማ የፈንዱ ዓላማ በዓለም ገበያ በሚከሰተው የነዳጅ ዋጋ ማደግ ምክንያት የሚያስፈልገውን ተጨማሪ ወጪ በመደጐም የነዳጅን ዋጋ ማረጋጋት ይሆናል ። ፈንዱ ምንጮች ፈንዱ ከሚከተሉት ምንጮች የሚሰበሰብ ይሆናል ፣ በዓለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ በመቀነሱ ምክንያት ከሚገኝ ተራፊ ሂሣብ ፣ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፱ሺ፩ ናው ኦዲተር በየዓመቱ ይመረ | ገጽ ፩ሺ፭፻፵፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፯ ሰኔ ፳፮ ቀን ፲፱፻ ዓም • ፪ . ለነዳጅ ዋጋ ማረጋጊያ እንዲውል ከሚገኝ የውጭ ዕርዳታ ፤ ይሆናል ። ፭ የፈንዱ ተሰብሳቢ ገንዘብ ፩ . የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት የአገር ውስጥ የነዳጅመሸጫ ዋጋ በሚወሰንበት ጊዜ ለነዳጅ መግዣና ለሌሎችም ጉዳዮች ታሳቢ ተደርገው በነበሩ ወጪዎች እና በትክክል በተደረገው ወጪ መካከል የሚኖረውን ልዩነት ለፈንዱ ሂሣብ ገቢ ያደርጋል ። ፪ . የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተገለፀውን ሂሣብ ለፈንዱ ገቢ የሚያደርገው በየሦስት ወሩ የሚደረገው የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ማስተ ካከያ ተግባራዊ ከተደረገበት ወር እ.ኤ.አ. አምስት የሥራ ቀናት ውስጥ ይሆናል ። ፮ : ስለክፍያዎች ከፈንዱ ሂሣብ ገንዘብ ወጪ ሆኖ የሚከፈለው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሲፈቅድ ይሆናል ። ፯ የገንዘብ ሚኒስትሩ ሥልጣን የገንዘብ ሚኒስትሩ ፣ ፈንዱ የሚቀመጥበትን ልዩ የባንክ ሂሣብ ይከፍታል ፣ የፈንዱን ሂሣብ ይይዛል ፣ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ሲፈቀድም ሥራ ላይ ያውላል ። የሂሳብ መዛግብት የፈንዱ የመዝገብና የሂሣብ አያያዝ ሥርዓት የፌዴራል መንግሥት የፋይናንስ አስተዳደር አዋጅን የሚከተል ይሆናል ። ፱ . ኦ ዲ ት የፈንዱ ሂሣብና መዛግብት መራሉ ። ፲ አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከሰኔ ፳፮ ቀን ፲፱፻፶፫ ዓም ጀምሮ የፀና አዲስ አበባ ሰኔ ፳፮ ቀን ፲፱፻፳ ዓ • ም • ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?