×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 23667

      Sorry, pritning is not allowed

የሲ.መ. ቁ . 23667
ዳኞች 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሠ
ዓብዱልቃድር መሐመድ 3. ›› ጌታቸው ምህረቱ
4. ›› መስፍን እቁበዮናስ
5. ወ / ት ሂሩት መለሰ
አመልካች፡- የኢት / የእህል ንግድ ድርጅት
ተጠሪ : - አቶ ግርማ ተገኝ
አቤቱታ መነሻ የሆነው የፌ / መ / ደረጃ ፍ / ቤት በመ / ቁ 14919
በዐ 4 / 02 / 98 የተሠጠው ውሣኔ ነው፡፡`
ተጠሪ ያላግባብ ከሥራ ስለተሠናበቱ ወደ ሥራ የመመለስ ክስ መስርተው ፍ / ቤቱ በ 14 / 11 / 96 ወደ ስራቸው እንዲመለሱ ወስኗል ፡፡ ነገር ግን አመልካች ወደ ስራቸው የመለሣቸው በ 7 / 4 / 97 በመሆኑ ውሣኔ ከተሠጠበት ጊዜ ጀምሮ ወደ ሥራ እስከተመለሱበት ጊዜ ያለው ደሞዝ እንዲከፈላቸው በ 11 / 9 / 97 በተፃፈ የክስ አቤቱታ ጠይቀዋል ፡፡ አመልካችም ወደ ስራ እንዲመለሱ ከተወሠነበት ጊዜ ጀምሮ ክስ
እስከቀረበበት ጊዜ ያለው ከ 10 ወር በላይ በመሆኑ ጥያቄው በይርጋ ይታገዳል
በማለት ተቃውሟል ፡፡ ፍ /
ቤቱ ግን ይርጋው ጊዜ መቆጠር መጀመር ያለበት ውሣኔ ከተሰጠበት ጊዜ ሣይሆን ወደ ስራ ከተመለሱበት ጊዜ ጀምሮ ነው በማለት የይርጋውን ጥያቄ ውድቅ አድርጎ አመልካች ለተጠሪ የ 4 ወራት ደሞዝ እንዲከፍል ውሣኔ ሠጥቷል ፡፡ ይግባኝ የቀረበለት የፌ / ከፍተኛ ፍ / ቤትም ይግባኙን ሠርዟል ፡፡
ችሎትም የይርጋውን ጊዜ አቆጣጠርን በተመለከተ ለመመርመር አቤቱታውን ለሠሰር አስቀርቦ ተጠሪም ቀርበው ችሎቱ የግራ ቀኙን የቃል ክርክር አድምጧል ፡፡
ፌደራል ቀና . . ፤
ትክክል ግልባጭ
ፊርማልፈፍ
ቀን 1 - 0 -12
5.0.ርጋው ከፍ ሲል እንደተገለፀው አመልካች ወደ ስራቸው እንዲመለሱ የተወሰነው በ 14 / 11 / 96 ነው ። በመሆኑም ተጠሪ ወደ ሥራቸው በመመለስ ደመወዝ የማግኘት መብታቸውን ያገኙት ይኸው ውሣኔ ከተሰጠበት ዕለት ጀምሮ ነው ፡፡ ነገር ግን ይህንን መብታቸውን ለመጠቀም የሚችሉት መቼ ነው የሚለውን ስንመለከት በአ / ቁ 377/96 አንቀፅ 163 ( 1 ) ሥር በአዋጁ በሌላ አኳኋን ካልተገለፀ በቀር የይርጋ ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው በመብቱ ለመጠቀም ከሚቻልበት ቀን ቀጥሎ ካለው ቀን ጀምሮ እንደሆነ ተመልክቷል ፡፡ ስለሆነም ተጠሪ ደመወዝ ለመጠየቅ የሚችሉት ወደ ስራ እንዲመለሱ ውሳኔ በተሠጠበት ወር ውስጥ የመ / ቤቱ የደመወዝ መክፈያ ከሚውልበት ቀን ቀጥሎ ካለው ቀን ጀምሮ ነው ፡፡
በተያዘው ጉዳይ ተጠሪ ክስ ያቀረቡት ደመወዝ እንዲከፈላቸው ስለሆነ የደመወዝ ክፍያ ጥያቄያቸውን ሊያቀርቡ የሚገባው የወሩ ደመወዝ ከሚከፈልበት ቀን ቀጥሎ ካለው ቀን ጀምሮ በ 6 ወራት ውስጥ ለመሆኑ ከአዋጁ አንቀፅ 162 ( 3 ) እንመለከታለን ፡፡ ተጠሪ የጠየቁት ወደ ስራ እንዲመለሱ ከተወሠነበት ቀን ጀምሮ ስራ እስኪጀምሩበት ጊዜ ያለውን የ 4 ወራት ደመወዝ ሲሆን ክስ የመሠረቱትም በ 11 / 09 / 97 ነው ፡፡ ከነዚህ የ 4 ወራት ደመወዝ ውስጥ የየወሩ ደመወዝ መጠየቅ ከሚቻልበት ቀን ጀምሮ ( የደመወዝ መክፈያ ቀን ) ክስ እስከቀረበበት ጊዜ ያለውና የ 6 ወር ጊዜ ያላለፈበት ደግሞ የህዳር ወር ደመወዝ ብቻ ነው ፡፡
በመሆኑም ፍ / ቤቶቹ
ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው ከውሣኔው ቀን ጀምሮ ሣይሆን ተጠሪ ወደ ስራ ገበታቸው ከተመለሱበት ቀን ጀምሮ ነው በማለት የ 4 ወራት ደመወዝ እንዲከፈላቸው መወሠናቸው ስህተት ነው ፡፡
የፌ / መ / ደረጃ ፍ / ቤት በመ / ቁ 14919 በዐ 4 / 02 / 98 የሰጠው ውሣኔና የፌ / ከፍተኛ ፍ / ቤት በመ / ቁ 42747 በ 18 / 04 / 98 የሠጠው ትዕዛዝ ተሻሽሏል ፡፡ አመልካች ለተጠሪ የህዳር ወር ደመወዛቸው ብቻ ይከፈላቸው ፡፡ ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ ፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል ፡፡ ይመለስ
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ፡፡
ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ግልባቼ *
ፊርዎ ... 18
1 - ( –ኘ ?

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?