×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር 123/1990 የመከላከያ ሠራዊት ማሻሻያ አዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አራተኛ ዓመት ቁጥር ፲፫ አዲስ አበባ ሰኔ ፳፫ ቀን ፲፱፻፲ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፩፻፳፫ ፲፱፻፲ ዓም የመከላከያ ሠራዊት ( ማሻሻያ ) ኣዋጅ . . . . . . . . . . . ገጽ ፯፻፫፱ አዋጅ ቁጥር ፩፻፳፫ / ፲፱፻፲ የመከላከያ ሠራዊት አዋጅን ለማሻሻል የወጣ አዋጅ የመከላከያ ሠራዊት አዋጅን ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፡ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) እና ( ፮ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የመከላከያ ሠራዊት ( ማሻሻያ ) አዋጅ ቁጥር ፩፻፳፫ / ፲፱፻፲ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ማሻሻያ የመከላከያ ሠራዊት አዋጅ ቁጥር ፳፯ / ፲፱፻፰፰ እንደሚከ ተለው ተሻሽሏል ፣ ፩ . የአንቀጽ ፬ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) ተሠርዞ ፡ የዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ) እና ( ፱ ) እንደቅደም ተከተላቸው ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) እና ( ) ሆነዋል ። ፪ . የአንቀጽ ፲፪ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) ተሠርዞ በሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) ተተክቷል ፤ “ . በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፱ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፪ ) የተመለከቱት የሥራ መሰናበቻ ዕድሜ ጣራዎች ለጡረታ ሕግ አፈጻጸም የጡረታ መገለይ ዕድሜ ሆነው ይቆጠራሉ ። ” ፫ አንቀጽ ፲፭ ተሠርዞ በሚከተለው አዲስ አንቀጽ ፲፭ ተተክቷል ፡ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ• ዥሺ፩ ገጽ ፯፻፲ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፫ ሰኔ ፳፫ ቀን ፲፱፻፲ ዓም . Federal Negarit Gazeta – No . 53 30 June , 1998 – Page 790 “ ፲፭ ሜዳይ ፡ ኒሻንና ሽልማት ማንኛውም የሠራዊቱ አባል በዚህ አዋጅ ወይም አግባብ ባላቸው ሌሎች ሕጐችና መመሪያዎች መሠረት ለፈጸመው አገልግሎትና ጀግንነት እንዲሁም ለአዲስ ግኝት ወይም የፈጠራ ሥራሜዳይ ፡ ኒሻን ወይም ሽልማት እንዲያገኝ ይደረጋል ። ” ፬ አንቀጽ ፳፩ ተሠርዞ በሚከተለው አዲስ አንቀጽ ፳፩ | ተተክቷል ፡ “ ፳፩ የግዴታ አገልግሎት አንድ የሠራዊት አባል ልዩ ሥልጠና ወይም ] ትምህርት እንዲያገኝ ከተደረገ ሥልጠናውን ወይም ትምህርቱን ከጨረሰ በኋላ ሥልጠናው ወይም ትምህርቱ የወሰደውን ጊዜ እጥፍ የማገልገል ግዴታ አለበት : ሆኖም የዚህ ዓይነቱ የግዴታ አገልግሎት ከአንድ ዓመት ሊያንስ አይችልም ። ” | ፭ አንቀጽ ፴፫ ተሠርዞ በሚከተለው አዲስ አንቀጽ ፴፫ | 5 ) Article 33 is deleted and replaced by the following new ተተክቷል ፡ st “ ፴፫• ስለምርመራና ክስ አመሠራረት ፩ አንድ ጉዳይ ወታደራዊ ፍ / ቤት ከመቅረቡ በፊት ጥልቅና | ገለልተኛ የሆነ ምርመራ መካሄድ አለበት ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት አንድ ጉዳይ ለምርመራ እንዳስፈላጊነቱ ለአንድ መርማሪ ፣ በቡድን እንዲሠሩ ለተመደቡ መርማሪዎች ወይም ለፖሊስ ሊመራ ይችላል ። ፫ የምርመራ ውጤቱ ክስ ለመመሥረት የሚያስችል ሆኖ ሲገኝ ጉዳዩ አግባብ ላለው ወታደራዊ ፍ / ቤት ይመራል ፡ ክሱን የሚከታተል ዐቃቤ ሕግም ይመደባል ። ” | ፮ ከአንቀጽ ፴፮ ቀጥሎ የሚከተለው ኣዲስ ክፍል ስድስት / 6 ) A new Part Six is added after Article 36 . ተጨምሯል ፡ “ ክፍል ስድስት ሜዳይ ፡ ሪባንና የምስክር ወረቀት የሚያስገኙ ሁኔታዎችና የተሸላሚዎች ልዩ መብቶች ፴፯ ሜዳዮች ፡ ሪባንና የምስክር ወረቀት ፩ ለመከላከያ ሠራዊት አባላት የሚሰጡ ሜዳዮች ፡ ሪባንና የምስክር ወረቀት የሚከተሉት ናቸው : ሀ ) የአድዋ ድል ሜዳይ : ለ ) የአውደ ውጊያ ጀግና ሜዳይ አንደኛ ደረጃ ፤ ሐ ) የአውደ ውጊያ ጀግና ሜዳይ ሁለተኛ ደረጃ ፡ መ ) የአውደ ውጊያ ጀግና ሜዳይ ሦስተኛ ደረጃ ፣ ሠ ) የትግል ተሳትፎ ሜዳይ ባለዘንባባ ፡ ረ ) የትግል ተሳትፎ ሜዳይ ያለዘንባባ ፡ ሰ ) የላቀ የሥራ ውጤት ሜዳይ : ሸ ) የውትድርና አገልግሎት ሜዳይ አንደኛ ደረጃ ፤ ቀ ) የውትድርና አገልግሎት ሜዳይ ሁለተኛ ደረጃ ፡ በ ) የውትድርና አገልግሎት ሜዳይ ሦስተኛ ደረጃ ፡ ተ ) ዓለምአቀፍ የሠላም ማስጠበቅ ሜዳይ ፡ ቸ ) የአውደ ውጊያ ቁስለኛ ሜዳይ ፡ ኀ ) የውትድርና አገልግሎት ሪባን ፡ ነ ) የውጊያ ተሳትፎ የምስክር ወረቀት ። ገጽ ፯፻፲፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ሰኔ ፳፫ ቀን ፲፱፻፲ ዓም Federal Negarit Gazeta - No . 53 30 June , 1998 - Page 791 ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከቱት ሜዳዮች ፣ ሪባንና የምስክር ወረቀት መጠን ፡ ቅርጽና ይዘት በሚኒስትሮች ምክር ቤት መመሪያ ይወሰናል ። ፴፰ : የአድዋ ድል ሜዳይ ፩ . የአድዋ ድል ሜዳይ ወደር የሌለው ጀግንነት በአውደውጊያ ለፈጸመ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ ወይም የሠራዊት አሀድ ወይም ቡድን የሚሰጥ የመጨረሻ ከፍተኛ የጀግና ሽልማት ነው ። ፪• የአድዋ ድል ሜዳይ የተሸለመ ሰው ፡ ሀ ) በሕይወት ያለ ከሆነ ብር ፳፭ሺ የአንድ ጊዜ ክፍያ ይሰጠዋል ፡ ከሞተም በጡረታ ሕግ በተመለከተው መጠን መሠረት ለወራሾቹ ብር ፳፭ሺ ይከፈላል ፡ ለ ) በብሔራዊ በዓል አከባበር ሥነ ሥርዓት | ወቅት ለከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣኖች በሚዘጋጀው ቦታ ይቀመጣል ፡ ሐ ) በርዕሰ ብሔሩ የተፈረመ ልዩ የመታወቂያ ወረቀት ይሰጠዋል ፡ መ ) በትውልድ ሥፍራው ትምህርት ቤት ፡ ሆስፒታል ፡ መንገድ ፡ አደባባይ ወይም ሌላ ተመሳሳይ መጠሪያ ሊሰየምለት ይችላል ። ፫ የአድዋ ድል ሜዳይ ሁለት ጊዜ የተሸለመ ሰው በፌዴራሉ ዋና ከተማ ትምህርት ቤት ፡ ሆስፒታል ፡ መንገድ : ድልድይ ፡ አደባባይ ወይም ሌላ ተመሳሳይ መጠሪያ በስሙ ሊሰየምለት ይችላል ፡ በተጨማሪም መታሰቢያ ሐውልት ሊቆምለት ይችላል ። ፬ . የአድዋ ድል ሜዳይ ተሸላሚ ለሆነ የሠራዊት አሃድ ወይም ቡድን ብር ፩፻ ሺ እና በርዕሰ ብሔሩ የተፈረመ ልዩ የምስክር ወረቀት ይሰጠዋል ። | ፭ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፪ ( መ ) እና ( ፫ ) ለሠራዊት አሃድና ቡድንም ተፈጻሚ ይሆናል ፡ ስለሆነም በትውልድ ሥፍራ ምትክ ጀግንነቱ የተፈጸመበት ሥፍራ ይሆናል ። ፴፱ የአውደ ውጊያ ጀግና ሜዳይ አንደኛ ደረጃ ትም ፩ . የአውደ ውጊያ ጀግና ሜዳይ አንደኛ ደረጃ በተሰለ ፈበት አውደ ውጊያ የዘወትር ወታደራዊ ግዳጅ አፈጻጸም ከሚጠይቀው በላይ እጅግ በጣም የሚያኮራ ጀግንነት ለፈጸመ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ ወይም የሠራዊት አሃድ ወይም ቡድን የሚሰጥ ሽልማት ነው ። ፪ . የአውደ ውጊያ ጀግና ሜዳይ አንደኛ ደረጃ የተሽለመ ሰው ፡ ሀ ) በሕይወት ያለ ከሆነ ብር ፳ ሺ የአንድ ጊዜ ክፍያ ይሰጠዋል ፡ ከሞተም በጡረታ ሕግ በተመለከተው መጠን መሠረት ለወራሾቹ ብር ፳ ሺ ይከፈላል ፡ በብሔራዊ በዓል አከባበር ሥነ ሥርዓት ወቅት ለከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣኖች በሚዘጋጀው ቦታ ይቀመጣል ፡ ሐ ) በጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ የተፈረመ ልዩ የመታወቂያ ወረቀት ይሰጠዋል ። ፫ የአውደ ውጊያ ጀግና ሜዳይ አንደኛ ደረጃ ሁለት ጊዜ የተሽለመ ሰው በትውልድ ሥፍራው ትምህርት ቤት ፡ ሆስፒታል ፡ መንገድ ፡ አደባባይ ወይም ሌላ ተመሳሳይ መጠሪያ በስሙ ሊሰየምለት ይችላል ። ገጽ ፯የጎ፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፫ ሰኔ ፳፫ ቀን ፲፱፻፲ ዓም Federal Negarit Gazeta No . 53 30 June , 1998 – Page 792 ዐ• የአውደ ውጊያ ጀግና ሜዳይ አንደኛ ደረጃ ሦስት ጊዜ የተሸለመ ወይም የአውደ ውጊያ ጀግና ሜዳይ አንደኛ ደረጃ እና የአድዋ ድል ሜዳይ የተሽለመ ሰው በፌዴራሉ ዋና ከተማ ትምህርት ቤት ፡ ሆሰፒታል ፡ መንገድ ፡ ኣደባባይ ወይም ሌላ ተመሳሳይ መጠሪያ በስሙ ሊሰየምለት ይችላል ። ፭ የአውደ ውጊያ ጀግና ሜዳይ አንደኛ ደረጃ ተሸላሚ ለሆነ የሠራዊት አሃድ ወይም ቡድን ብር ዥ ሺ እና በጦርኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ የተፈረመ ልዩ የምስክር ወረቀት ይሰጣል ። ፮ : የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) እና ( ፱ ) ለሠራዊት አሃድና ቡድንም ተፈጻሚ ይሆናል ፡ ስለሆነም በትውልድ ሥፍራ ምትክ ጀግንነቱ የተፈጸመበት ሥፍራ ይሆናል ። ፵ የአውደ ውጊያ ጀግና ሜዳይ ሁለተኛ ደረጃ ፩ የአውደ ውጊያ ጀግና ሜዳይ ሁለተኛ ደረጃ በተሰለፈበት አውደ ውጊያ የዘወትር ወታደራዊ ግዳጅ አፈጻጸም ከሚጠይቀው በላይ በጣም የሚያኮራ ጀግንነት ለፈጸመ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ ወይም የሠራዊት አሃድ ወይም ቡድን የሚሰጥ ሽልማት ነው ። ፪ . የአውደ ውጊያ ጀግና ሜዳይ ሁለተኛ ደረጃ የተሸለመ ሀ ) በሕይወት ያለ ከሆነ ብር ፲፭ ሺ የአንድጊዜ ክፍያ ይሰጠዋል ፡ ከሞተም በጡረታ ሕግ በተመለ ከተው መጠን መሠረት ለወራሾቹ ብር ፲፭ ሺ ይከፈላል ፡ ለ ) በብሔራዊ በዓል አከባበር ሥነ ሥርዓት ወቅት ለከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣኖች በሚዘ ጋጀው ቦታ ይቀመጣል ። ሐ ) በጠቅላይ ኤታማዦር ሹም የተፈረመ ልዩ የመታ ወቂያ ወረቀት ይሰጠዋል ። ፫• የአውደ ውጊያ ጀግና ሜዳይ ሁለተኛ ደረጃ ተሸላሚ ለሆነ የሠራዊት አሃድ ወይም ቡድን ብር ፶ ሺ እና | በጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ የተፈረመ ልዩ የምስክር ወረቀት ይሰጣል ። ፴፩ የአውደ ውጊያ ጀግና ሜዳይ ሦስተኛ ደረጃ ፩ የአውደ ውጊያጀግና ሜዳይ ሦስተኛ ደረጃ በተሰለፈበት | 41 . The Medal of Heroism 3 Rank አውደ ውጊያ የዘወትር ወታደራዊ ግዳጅ አፈጻጸም ከሚጠይቀው በላይ የሚያኮራ ጀግንነት ለፈጸመ ኢትዮ ጵያዊ ግለሰብ ወይም የሠራዊት ኣሃድ ወይም ቡድን የሚሰጥ ሽልማት ነው ። ፪ የአውደ ውጊያ ጀግና ሜዳይ ሦስተኛ ደረጃ የተሸለመ ሀ ) በሕይወት ያለ ከሆነ ብር ፲ ሺ የአንድ ጊዜ ክፍያ ይሰጠዋል ፡ ከሞተም በጡረታ ሕግ በተመለ ከተው መጠን መሠረት ለወራሾቹ ብር ፲ ሺ . ይከፈላል ። ለ ) በጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ የተፈረመ ልዩ የመ ታወቂያ ወረቀት ይሰጠዋል ። ፫ የአውደ ውጊያ ጀግና ሜዳይ ሦስተኛ ደረጃ ሦስት ጊዜ ወይም ከዚያ በላይ የተሸለመ ሰው በብሔራዊ በዓል አከባበር ሥነ ሥርዓት ወቅት በተለይ በሚወሰንለት የክብር ሥፍራ ይቀመጣል ። ፬ . የአውደ ውጊያጀግና ሜዳይ ሦስተኛ ደረጃ ተሸላሚለሆነ የሠራዊት አሃድ ወይም ቡድን ብር ፶ ሺ እና በጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ የተፈረመ ልዩ የምስክር ወረቀት ይሰጣል ። ገጽ ፯የን ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፫ ሰኔ ፳፫ ቀን ፲፱፻፲ ዓ . ም . Federal Negarit Gazeta No . 53 30 June , 1998 – Page 793 ፴፪• የትግል ተሳትፎ ሜዳይ ባለዘንባባ ፩ የትግል ተሳትፎ ሜዳይ ባለዘንባባ በኢትዮጵያ ሠላምና ዲሞክራሲን ለማስፈን ከደርግ ፡ ኢሠፓ መንግሥት ጋር ከ፲፱፻፷፯ ዓም እስከ ግንቦት ፳ ቀን ፲፱፻፳፫ ዓም ድረስ በትጥቅ ትግሉ ከአሥር ዓመት ያላነሰ ተሳትፎ ላለው ታጋይ የሚሰጥ ሽልማት ነው ። ፪• የትግል ተሳትፎ ሜዳይ ባለዘንባባ የተሸለመ ሰው በጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ የተፈረመ ልዩ የመታ ወቂያ ወረቀት ይሰጠዋል ። ፴፫ የትግል ተሳትፎ ሜዳይ ያለዘንባባ ፩ . የትግል ተሳትፎ ሜዳይ ያለዘንባባ በኢትዮጵያ ሠላምና ዲሞክራሲን ለማስፈን ከደርግ ኢሠፓ መንግሥት ጋር ከ፲፱፻፷፯ ዓ . ም . እስከ ግንቦት ፳ ቀን ፲፱፻ዥ፫ ዓም ድረስ በትጥቅ ትግሉ ከአሥር ዓመት በታች ተሳትፎ ላለው ታጋይ የሚሰጥ ሽልማት ነው ። ፪• የትግል ተሳትፎ ሜዳይ ያለዘንባባ የተሽለመ ሰው በጠቅላይ ኤታማገገር ሹሙ የተፈረመ ልዩ የመታ ወቂያ ወረቀት ይሰጠዋል ። ፴፬ የላቀ የሥራ ውጤት ሜዳይ ፩ : የላቀ የሥራ ውጤት ሜዳይ በኣእምሮ ሥራ ወይም 144 . The Medal of Distinguished Labour በፈጠራ ወይም በማናቸውም መስክ ለመከላከያ ሠራዊት ተልዕኮ መሳካት የላቀና ወደር የሌለው ውጤት ላስገኘ ሰው ወይም የሠራዊት አሃድ ወይም ቡድን የሚሰጥ ሽልማት ነው ። ፪ . የላቀ የሥራ ውጤት ሜዳይ የተሸለመ ሰው : ሀ ) ብር ፲ ሺ የአንድ ጊዜ ክፍያ ይሰጠዋል ፡ ለ ) በብሔራዊ በዓል አከባበር ሥነ ሥርዓት ወቅት ለከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣኖች በሚዘ ጋጀው ቦታ ይቀመጣል ፡ ሐ ) በሀገር መከላከያ ሚኒስትሩ የተፈረመ ልዩ የመታወቂያ ወረቀት ይሰጣል ። _ ፫ የላቀ የሥራ ውጤት ሜዳይ ለተሸለመ የሠራዊት አሃድ ወይም ቡድን ብር ፶ ሺ እና በመከላከያ ሚኒስትሩ የተፈረመ ልዩ የምስክር ወረቀት ይሰጣል ' ። ፵፭ የውትድርና አገልግሎት ሜዳይ አንደኛ ደረጃ የውትድርና አገልግሎት ሜዳይ አንደኛ ደረጃ በሥነ | 45 . The Medal of Military Service 1 Rank ምግባሩና በወታደራዊ ሥነ - ሥርዓት የጐላ እንከን የሌለ በትና በመከላከያ ሠራዊት ውስጥ ከሃያ አምስት ዓመታት ላላነስጊዜ ላገለገለ የሠራዊት አባል የሚሰጥ ሽልማት ነው ። ፴፮ የውትድርና አገልግሎት ሜዳይ ሁለተኛ ደረጃ የውትድርና አገልግሎት ሜዳይ ሁለተኛ ደረጃ በሥነ | 46 . The Medal of Military Service 2nd rank ምግባሩና በወታደራዊ ሥነ - ሥርዓት የጐላ እንከን የሌለ በትና በመከላከያ ሠራዊት ውስጥ ከአሥራ አምስት ዓመት ላላነሰ ጊዜ ላገለገለየሠራዊት አባል የሚሰጥ ሽልማት ነው ። የውትድርና አገልግሎት ሜዳይ ሦስተኛ ደረጃ የውትድርና አገልግሎት ሜዳይ ሦስተኛ ደረጃ በሥነ | 47 , ምግባሩና በወታደራዊ ሥነ - ሥርዓት የጐላ እንከን የሌለ በትና በመከላከያ ሠራዊት ውስጥ ከአሥር ዓመት ላላነሰ ጊዜ ላገለገለ የሠራዊት ኣባል የሚሰጥ ሽልማት ነው ። ፵፰ ዓለም አቀፍ የሰላም ማስጠበቅ ሜዳይ 6 - ዓለም አቀፍ የሠላም ማስጠበቅ ሜዳይ ከኢትዮጵያ | 48 The Medal of International Peace Keeping ውጭ ከጓ ቀናት ላላነሰ በዓለምአቀፍና አህጉራዊ | የሠላም ማስጠበቅ ተግባር ለተሳተፈ ሰው የሚሰጥ ሽልማት ነው ። ፪ : ዓለም አቀፍ የሠላም ማስጠበቅ ሜዳይ የተሸለመ ሰው በጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ የተፈረመ ልዩ የመታ ወቂያ ወረቀት ይሰጠዋል ። ገጽ Lየ10 ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፫ ሰኔ ፳፫ ቀን ፲፱፻፲ ዓ . ም Federal Negarit Gazeta - No . 53 30 June , 1998 – Page 794 ሀ• የአውደ ውጊያ ቁስለኛ ሜዳይ ፩ : የአውደ ውጊያ ቁስለኛ ሜዳይ በአውደ ውጊያ ተሰልፎ | ) The Medal of the Wounded is an award that may be የመቁሰል አደጋ ለደረሰበት ሰው የሚሰጥ ሽልማት ፪• የአውደ ውጊያ ቁስለኛ ሜዳይ የተሸለመ ሰው በክፍለ ጦር ወይም በኮር አዛዥ ወይም በተመጣጣኝ ደረጃ የተፈረመ ልዩ የመታወቂያ ወረቀት ይሰጠዋል ። ፃ የውትድርና አገልግሎት ሪባን የውትድርና አገልግሎት ሪባን ለሕገመንግሥቱ ታማኝ በመሆን በመከላከያ ሠራዊት ውስጥ ለተሰጠ ለእያንዳንዱ | አምስት ዓመት አገልግሎት የሚሰጥ ሽልማት ነው ። ፴፩ የውጊያ ተሳትፎ የምስክር ወረቀት የውጊያ ተሳትፎ የምስክር ወረቀት በመንግሥት በታወቀና በታወጀ ወታደራዊ ስምሪት ( ዘመቻ ) ለተሳተፈ ሰው ወይም | የሠራዊት አሃድ ወይም ቡድን የሚሰጥ ሽልማት ነው ። | ፲፪• የሜዳይ ተሸላሚ የሚያገኘው ተጨማሪ ልዩ መብት በዚህ አዋጅ ሌሎች አንቀጾች የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ፡ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፴፯ ( ፩ ) ( ሠ ) ( ሰ ) ፡ ( ተ ) ወይም ( ቸ ) የተመለከተውን ማንኛውም ሜዳይ የተሸለመ ሰው ፡ ፩ . በመንግሥት ሆስፒታሎችና የሕክምና ተቋሞች ውስጥ ነፃ ሕክምና ያገኛል ፡ ፪ . በመንግሥት የትምህርት ተቋሞች ውስጥ ለመማር ቅድሚያ ያገኛል ፡ ፫ : በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ፡ ድርጅቶችና ተቋሞች ውስጥ ችሎታው ለሥራ መደቡ ተስማሚ ሆኖ ሲገኝ የመቀጠር ቅድሚያ ይሰጠዋል ። ለሜዳይ ሽልማት የሚያበቃ ሥራ ሠርቶ ስለሞተ ሰው | 53 . Posthumous Award of Medals ፩ ለሜዳይ ሽልማት የሚያበቃ ሥራ ሠርቶ የሞተ ሰው አግባብ ያለው ሜዳይ በስሙ ይመዘገባል ። ፪ ሜዳዩ ለታላቅ ልጁ ይሰጣል ። ልጅ ከሌለው ለባለቤቱ ፣ ባለቤት ከሌለው አግባብ ባለው የውርስ ሕግ መሠረት ለውርስ ባለመብቱ ይሰጣል ። ፲፬ ከውጪ አገር ሜዳይ ወይም ሌላ ሽልማት ስለመቀበል ማንኛውም የመከላከያ ሠራዊት አባል ከአገር መከላከያ | 54 . Receiving Foreign Medals or Other Prizes ሚኒስቴር ፈቃድ ሳያገኝ ከውጭ አገር ሜዳይ ወይም ሽልማት ሊቀበል አይችልም ። H፭ ሜዳይ ፡ ሪባን ወይም የምስክር ወረቀት መልሶ ስለመውሰድ ተሸላሚው ፡ ፩ ሜዳዩ ፡ ሪባኑ ወይም የምስክር ወረቀቱ የተሰጠው በተሳሳተ ማስረጃ መሆኑ ሲታወቅ ፡ ወይም ፪ - በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ከቁጥር ፪፻፱ ፪፻፷፭ የተመለ ከቱትን ወንጀሎች መፈጸሙ በፍ ቤት ውሣኔ ሲረጋገጥ ፡ የተሰጠው ሜዳይ ፡ ሪባን ወይም የምስክር ወረቀት ይወሰድበታል ። ፴፮ የሜዳዮች ደረጃ ቅደም ተከተል የሜዳዮች ደረጃ ቅደም ተከተል በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፴፯ ( ፩ ) | በተመለከተው ዝርዝር ቅደም ተከተል መሠረት ይሆናል ። ገጽ ፯፻፲፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፫ ሰኔ ፳፫ ቀን ፲፱፻፵ ዓ . ም . Federal Negarit Gazeta – No . 53 30ጮ June , 1998 - Page 795 ፫ ሃ፯ የሜዳዮችና ሪባኖች አሰጣጥ ሥርዓትና አለባበስ በዚህ አዋጅ የተመለከቱት ሜዳዮችና ሪባኖች አሰጣጥ ሥርዓትና አለባበስ በሚኒስትሮች ምክር ቤት መመሪያ ይወሰናል ። ፯ . የአዋጁ የቀድሞው ክፍል ስድስት ክፍል ሰባት ሆኖ አንቀጽ ፴፯ ፴፬ እንደ ቅደም ተከተላቸው አንቀጽ ፵፰ ፰ ሆነዋል ። አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከሰኔ ፳፫ ቀን ፲፱፻፲ ዓም ጀምሮ የጸና ይሆናል | አዲስ አበባ ሰኔ ፳፫ ቀን ፲፱፻፲ ዓም• ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃን ሰላም ማተሚያ ድርጅት

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?